የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የዚህ ጥናት ዓላማ ከእያንዳንዱ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ጋር በሚገባ እንድትተዋወቅ ለማድረግና የመጽሐፉን እውነቶች ከዘመናችን ጋር ለማዛመድ በመጣር እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን ያለውን መልእክት ለመረዳት ነው። የእግዚአብሔርን ቃል ማወቅ ከሕይወታችንም ጋር ማዛመድ አስፈላጊ እንደሆነ ልብ በል። የእግዚአብሔርን ቃል ባናጠናና በግል ከሕይወታችን ጋር ባናዛምደው፥ ከእግዚአብሔር ጋር በምናደርገው ጉዞ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያስከትልብናል፤ መንፈሳዊ ሕይወታችንም ይጠወልጋል። ይህ ጥናት ከእያንዳንዱ ተማሪ ብዙ ሥራን የሚጠይቅ ነው፤ ዳሩ ግን ከራስህ ሕይወት ጋር በማዛመድ ጥያቄዎቹን ሁሉ በጥንቃቄ ብትመልስና የሚሰጡህን ሥራዎች በሙሉ ብትሠራ፥ ብሉይ ኪዳንን በተሻለ መንገድ በመረዳት ከእግዚአብሔር ጋር ያለህ እርምጃ በይበልጥ ዕድገት ከማሳየቱም ሌላ፥ በሚገባ በምታውቀውና በተወሰነ የእግዚአብሔር ቃል ክፍል ላይ ከማተኮር ይልቅ ለሁሉም ክፍል ፍቅር ይኖርህና እንዴት ልትጠቀምበት እንደሚገባ ታውቃለህ። ሮሜ 15፡4 እንዲህ ይላል፡«በመጽናትና መጻሕፍት በሚሰጡት መጽናናት ተስፋ ይሆንልን ዘንድ አስቀድሞ የተጻፈው ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፎአልና።»

የጥያቄዎቹን መልሶች በደብተር ጻፍ። የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ከሌለህ ለጥናትህ ይረዳህ ዘንድ ለመግዛት ሞክር። አዲሱ ትርጒም የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስና የእንግሊዝኛ መጽሓፍ ቅዱስ ካለህ፥ በተጨማሪ ከእነርሱም አንብብ።

በትምህርቶቹ ውስጥ በርካታ ማብራሪያ ጥቅሶች ተሰጥተዋል። ከተሰጡት ጥቅሶች መካከል «ተመልከት» ተብለው የተጻፉትን ሁሉ መመልከት አስፈላጊ ነው። «ተመልከት» የሚል ትእዛዝ ያልተሰጠባቸውን ግን ጊዜ ካለህ ልትመለከታቸው ትችላለህ፤ አለበለዚያም ለሌላ የጥናትህ ጊዜ የሚጠቅሙህ ይሆናሉ።

የዚህ ጥናት አንዱ ግብ ተማሪው ብሉይ ኪዳንን በሙሉ እንዲያጠና ለመርዳት ነው። ስለዚህ ለአንድ ተማሪ የተሰጠውን የንባብ ክፍል ሁሉ አጠናቅቆ ማንበብ በጣም አስፈላጊ ነው።

በጥናቱ ውስጥ የተካተቱትን ጥያቄዎች ከመስራትዎ በፊት፣ መመሪያውን ጨምሮ በጥያቄዎቹ የፊት ገጽ ላይ የሚጠየቁትን ትክክለኛ ስምዎን (ወይም የብዕር ስምዎን) እና ትክክለኛ የኢ-ሜይል አድራሻዎን መሙላትዎን አይዘንጉ። ትክክለኛ የኢ-ሜይል አድራሻ እንዲሞሉ የተጠየቁበት ምክንያት ውጤትዎ የሚላከው በዚሁ አድራሻ ስለሆነ ነው፡፡ ጥያቄዎቹን ሰርተው ሲያበቁ “submit” የሚለውን ቁልፍ ይጫኑ። አንዳንድ ጊዜ “Google” ጥያቄዎቹን የሰራው ኮምፒውተር ወይም ሰው መሆኑን ለማጣራት የሴኪውሪቲ ጥያቄዎችን ሊጠይቆት ይችላል። “Submit” የሚለውን ቁልፍ ከተጫኑ በኋላ “view your score” የሚለውን ቁልፍ በመጫን ውጤትዎን እና የተሳሳቱትን ጥያቄ ግብረ መልስ (feedback) ማየት ይችላሉ። በጥያቄዎቹ ላይ የሚያነሱት ሃሳብ ካለ በሚከተለው ኢ-ሜይል ይላኩልን። tsegaewnet@gmail.com

የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

፩. ኦሪት ዘፍጥረት

 1. ዘፍጥረት 1-2 የዓለም አፈጣጠር
 2. የአዳምና የሔዋን ኃጢአት (ከዘፍ. 3)
 3. ዘፍጥረት 4-11 የኃጢአት በመላው ዓለም መሠራጨት
 4. የአብርሃም ታሪክ (ዘፍጥረት 12-24)
 5. ዘፍጥረት 25-36 የይስሐቅና የያዕቆብ ታሪክ
 6. ዘፍጥረት 37-50 የዮሴፍ ታሪክ

፪. ኦሪት ዘጸአት

 1. የእግዚአብሔር ሕዝብ በባርነት ቀንበር ሥር መሆን እና እግዚአብሔር ሕዝቡን ከባርነት ለማውጣት መሪ መጥራቱ (ዘጸአት 1-4)
 2. የእግዚአብሔር ሕዝብ ነጻነት (ዘጸ. 5-12)
 3. ዘጸአት 13-18
 4. ዘጸአት 19-24
 5. ዘጸአት 25-40

፫. ኦሪት ዘሌዋውያን

 1. ኦሪት ዘሌዋውያን 1-10
 2. ዘሌዋውያን 11-22
 3. ዘሌዋውያን 23-27

፬. ኦሪት ዘኁልቁ

 1. ዘኍልቁ 1-12
 2. ዘኍልቁ 13-21
 3. ዘኁልቁ 22-36

፭. ኦሪት ዘዳግም

 1. ዘዳግም 1-11
 2. ዘዳግም 12-26
 3. ዘዳግም 27-34
 4. የፔንታቱክ ክለሣ

፮. መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ

 1. ኢያሱ 1-12
 2. ኢያሱ 13-24
 3. የመጽሐፈ ኢያሱ ዋና ትምህርቶች

፯. መጽሐፈ መሳፍንት

 1. መሳፍንት 1-16
 2. መሳፍንት 17-21
 3. የመጽሐፈ መሳፍንት ዋና ዋና ትምህርቶች

፰. መጽሐፈ ሩት

 1. መጽሐፈ ሩት (1-4)
 2. የመጽሐፈ ሩት ዋና ዋና ትምህርቶች

፱. መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ

 1. የሳሙኤል መወለድና ጥሪ (1ኛ ሳሙ. 1-3)
 2. 1ኛ ሳሙ.4-7
 3. ሳኦል የእስራኤል ንጉሥ ይሆን ዘንድ ተመረጠ (1ኛ ሳሙ. 8-11)
 4. 1ኛ ሳሙኤል 13-15
 5. በዳዊትና በሳኦል መካከል የቀረበ ንጽጽር (1ኛ ሳሙ. 16-20)
 6. 1ኛ ሳሙኤል 21-31
 7. የ1ኛ ሳሙኤል ዋና ዋና ትምህርቶች

፲. መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ

 1. 2ኛ ሳሙኤል 1፡1-5፡5
 2. 2ኛ ሳሙኤል 5፡6-12፡31
 3. 2ኛ ሳሙኤል 13-19
 4. 2ኛ ሳሙኤል 20-24
 5. የ2ኛ ሳሙኤል ዋና ዋና ትምህርቶች

፲፩. መጽሐፈ መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ

 1. የሰሎሞን ንጉሥ መሆንና የታላቅነቱ ማስረጃዎች (1ኛ ነገሥት 1-10)
 2. የሰሎሞን ውድቀት (1ኛ ነገሥት 11)
 3. 1ኛ ነገሥት 12-16
 4. 1ኛ ነገሥት 17-22

፲፪. መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ

 1. 2ኛ ነገ. 1፡1-8፡15
 2. 2ኛ ነገሥት 8፡16-12፡21
 3. 2ኛ ነገሥት 13-17
 4. 2ኛ ነገሥት 18-25
 5. መጽሐፈ ነገሥት ከአዲስ ኪዳን ጋር ያለው ግንኙነት

፲፫. መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ እና ካልዕ

 1. 1ኛ ዜና 1 እስከ 2ኛ ዜና መጨረሻ

፲፬. መጽሐፈ ዕዝራ

 1. ዕዝራ 1-6
 2. ዕዝራ 7-10
 3. የመጽሐፈ ዕዝራ ዋና ዋና ትምህርቶች

፲፭. መጽሐፈ ነህምያ

 1. ነህምያ 1-4
 2. ነህምያ 5-10
 3. ነህምያ 11-13
 4. የመጽሐፈ ነህምያ ዋና ዋና ትምህርቶች

፲፮. መጽሐፈ አስቴር

 1. አስቴር 1-6
 2. አስቴር 7-12
 3. የመጽሐፈ አስቴር ዋና ትምህርት
 4. የታሪክ መጻሕፍት ክለሳ

ማሣሠቢያ፡- ይህ የብሉይ ኪዳን ጥናት ማብራሪያ ለጊዜው መጽሐፈ ኢዮብ፣ መዝሙረ ዳዊት እና መጽሐፈ ምሳሌን ያላካተተ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ በቀጣይ፣ በተቻለ ፍጥነት እነዚህን ቅዱሳት መጽሐፍት ለማካተት እንጥራለን፡፡ እስከዛው፣ የመጽሐፈ መክብብ ጥናትን እና ቀጣዮቹን የብሉይ ኪዳን ቅዱሳት መጻሕፍት በማጥናት መንፈስዎን ይመግቡ፡፡ 

፲፯. መጽሐፈ ኢዮብ

 1. የመጽሐፈ ኢዮብ መግቢያ
 2. የመጽሐፈ ኢዮብ ዓላማ
 3. ከመጽሐፈ ኢዮብ የምናገኛቸው ልዩ ትምህርቶች

፲፰. መዝሙረ ዳዊት

፲፱. መጽሐፈ ምሳሌ

፳. መጽሐፈ መክብብ

 1. መክብብ 1-6
 2. መክብብ 7-12

፳፩. መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን

፳፪. ትንቢተ ኢሳይያስ

 1. ኢሳይያስ 1-6
 2. ኢሳይያስ 7-12
 3. ኢሳይያስ 12-23
 4. ኢሳይያስ 24-39
 5. ኢሳይያስ 40-49
 6. ኢሳይያስ 50-66

፳፫. ትንቢተ ኤርምያስ

 1. ኤርምያስ 1-6
 2. ኤርምያስ 7-17
 3. ኤርምያስ 18-25
 4. ኤርምያስ 26-36
 5. ኤርምያስ 37-45
 6. ኤርምያስ 46-52

፳፬. ሰቆቃው ኤርምያስ

፳፭. ትንቢተ ሕዝቅኤል

፳፮. ትንቢተ ዳንኤል

፳፯. ትንቢተ ሆሴዕ

፳፰. ትንቢተ አሞጽ

፳፱. ትንቢተ ሚክያስ

፴፩. ትንቢተ ኢዮኤል

፴፪. ትንቢተ አብድዩ

፴፫. ትንቢተ ዮናስ

፴፬. ትንቢተ ናሆም

፴፭. ትንቢተ ዕንባቆም

፴፮. ትንቢተ ሶፎንያስ

፳፯. ትንቢተ ሐጌ

፴፰. ትንቢተ ዘካርያስ

፴፱. ትንቢተ ሚልክያስ