የመንፈሳዊ ስጦታዎች ትምህርት ማጠቃለያ

ጥያቄ፡- በ1ኛ ቆሮ. 14፡1 ላይ ታላላቅ መንፈሳዊ ስጦታዎችን በብርቱ እንድንፈልግ ተነግርናል። ሀ) ታላላቅ ስጦታዎች እንደሆኑ የምታምናቸውን ጥቀስ። ለ) ከእነዚህ ስጦታዎች አንዱን በማግኘት ምን ለማድረግ የምትችል ይመስልሃል? 

ታላላቅ ስጦታዎችን እንዴት መፈለግ እንችላለን?

እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን ከሰጠው ውድ ስጦታዎች አንዳንዶቹ መንፈሳዊ ስጦታዎች ናቸው። በእነዚህ ስጦታዎች ቤተ ክርስቲያን በውስጧ ያሉትንና ዓለምን ታገላግላለች። መንፈሳዊ ስጦታዎች ቤተ ክርስቲያን የኢየሱላ እጆች፥ አፎችና፥ እግሮች ሆና እንድታገለግል ያደርጋሉ። መንፈሳዊ ስጦታዎች በሙሉ እጅግ አስፈላጊዎች ናቸው። ከመንፈሳዊ ስጦታዎች እንዳንዶቹ እንኳ ቢጐድሉ ብዙ ሳይቆዩ ቤተ ክርስቲያን መፍገምገምና መንፈሳዊ ትጋቷን መጣል ትጀምራለች። ነገር ግን ከሌሎች የላቁና የተሻሉ እግዚአብሔር በልባችን ሸክምን ካኖረ የበለጠ ልንፈልጋቸው የሚገቡ አንዳንድ መንፈሳዊ ስጦታዎች እንዳሉ ተነግሮናል። በእግዚአብሔር ዓይን ከሌሎች የላቁ የሚባሉ መንፈሳዊ ስጦታዎች የትኞቹ መሆናቸውን እንዴት እናውቃለን? አስታውሱ መፈለግ ያለብን በሰው ዓይን የላቁ የሚባሉ መንፈሳዊ ስጦታዎችን አይደለም። ሰው ትኩረት የሚያደርገው ታላቅና መንፈሳዊ በሚመስል ውጫዊ ነገር ላይ ነው። እና ብዙ ጊዜ የምንፈልገው አስደናቂ የሆኑ ነገሮችን ነው። እግዚአብሔር ታላቅ የሚለው ቀን ብዙ ጊዜ እኛ ከምንላው የተለየ ነው። 

አንድ መንፈሳዊ ስጦታን ታላቅ የሚያደርጉት ነገሮች ምንድን ናቸው? መንፈሳዊ ስጦታዎች የሚሰጡት ለጋራ ጥቅም መሆኑን ካስታወስን ታላላቹ መንፈሳዊ ስጦታዎች የክርስቶስን አካል ለማነጽ ከሁሉም በላይ የሚጠቅሙት ናቸው። ጳውሎስ በልሳን ከመናገር ስጦታ ትንቢት እንደሚበልጥ የተናገረው ለዚህ ነው። በቤተ ክርስቲያን ለሚገኙ ሁሉ የበለጠ የሚጠቅም ስለሆነ የተሻለ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ ከሁሉ የላቁ ስጦታዎች የሚላቸው ስት ለጦታዎች አሉ። 

1. ወንጌልን እንዲሠራጭና ቤተ ክርስቲያን እንድትቆረቆር የሚያስችሉ መንፈሳዊ ስጦታዎች (ሐዋርያነትና ወንጌላዊነት)። እነዚህ ስጦታዎች ቤተ ክርስቲያን እንድትስሩሩ የባሕል ልዩነት ሳያግዳት ወንጌል ወዳልደረሰባቸው ሥፍራዎች ወንጌልን እንድታዳረስ ያስችሏታል። 

ጥያቄ፡– ይህ ስጦታ በቤተ ክርስቲያንህ እንዴት እየተፈጸመ እንዳለ ምሳሌ ስጥ። ይህ ስጦታ እጅግ ጠቃሚና ፍጹም የማይታለፍ ለጦታ የሆነው ለምንድን ነው? 

2. የቤተ ክርስቲያን አባላት በእግዚአብሔር ቃል እውቀትና በቤተ ክርስቲያንና በማኅበረሰባቸው መካከል እግዚአብሔርን በማገልገል ችሎታ እንዲያድጉ የሚረዱ ስጦታዎች (የማስተማር፥ የትንቢትሩ የስብከት)። 

3. ለቤተ ክርስቲያንና ለጎስቋላ ሰዎች ሥጋዊ ችግሮች ክብካቤ ለመስጠት የሚረዱ ክርስቲያናዊ ፍቅርን የሚያንጸባርቁ መንፈሳዊ ስጦታዎች ፈውስና ምሕረት ማድረግ) 

ጥያቄ፡- እነዚህ ሦስት ዓይነት ስጦታዎች ለቤተ ክርስቲያን አስፈላጊ የሆኑት ለምንድን ነው? 

በልሳናት መናገር፥ የተነገረውን መተርጐም፥ ተአምራትን ማድረግና አስተዳደር ወዘተ… ለእነዚህ ዋነኛ የመንፈሳዊ ስጦታዎች ድጋፍ ሰጭ ናቸው። አስፈላጊ ቢሆኑም እንኳ ከሁሉ የላቁ ስጦታዎች ግን አይደሉም። እነዚህ ስጦታዎች ብዙ ጊዜ ድንቀኛ ቢሆኑም እንኳ የቤተ ክርስቲያን መሠረተች ግን አይደሉም። ያለ ዋንኞቹ ስጦታዎች ቤተ ክርስቲያን ልትኖር አትችልም። እዚህ ስጦታዎች ባይኖሩአትም እንኳ ቤተ ክርስቲያን ያለማቋረጥ መሥራትና ዓላማዋን መፈጸም ትችላለች። ስለዚህ እጅግ አስፈላጊ ባልሆኑ አንዳንድ ስጦታዎች ላይ ስናተኩር ውስጣዊ አሳባችንን ልንመረምር ይገባል። መንፈሳዊ ስጦታዎችን የምንፈልገው በእርግጥ በተሻለ ሁኔታ ለማገልገል ነውን? ወይስ በትዕቢትና በኩራት እራሳችንን ለመገንባት ነው? 

ታላላቅ ስጦታዎችን እንዴት እናገኛለን? 

1. መንፈሳዊ ስጦታዎችን እርሱ እንደ ፈለገ ማከፋፈል የመንፈስ ቅዱስ ሉዓላዊ ደስታ መሆኑን ማስታወስ አለብን። ሆኖም ቀን እግዚአብሔር ከሰጠን መብቶች አንዱ መንፈሳዊ ስጦታን ይሰጠን ዘንድ መንፈስ ቅዱስን መጠየቅ ነው። ውስጣዊ ዓላማችን ትክክል ከሆነ ብዙ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ጥያቂዎቻችንን ይመልሳል። 

2. ወደ ቤተ ክርስቲያንና ወደ ዓለም ችግሮች መመልከት አለብን። ለእነዚህ ችግሮች በሚያስፈልጉ መፍትሔዎች ላይ በመመሥረት ከሁሉ በላይ አስፈላጊ የሆኑ ስጦታዎች የትኞቹ እንደሆኑ እንገመግማለን። 

3. ልባችንን በጥንቃቄ መመርመር አለብን። በአንድ ነገር ለመሳተፍ እዚአብሔር ፍላጐትን ሰጥተሃልን? መንፈስ ቅዱስ ይህን ፍላጐትህን ተጠቅሞ የላቀ ስጦታን እንድትሻ እያደረገህ ነውን? 

4. አንድ ስጦታ የምንፈልግበት ውስጣዊ ዓላማችን ምንድን ነው? መንፈሳዊ ስጦታዎችን የተቀበልን ቢሆንና ትክክለኛ ዓላማ ሳይኖረን ፍጻሜያችን ቤተ ክርስቲያንን መጉዳት ይሆናል። ለምሳሌ አንዳንድ ሰዎች የመጋቢነት አገልግሎት ለመያዝ የሚፈልጉት ከዚህ ኃላፊነት የሚገኘውን ክብር ለመውሰድ ነው። በዚህ መንፈስ መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ቢገቡና ከዚያም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አገልግሎት ማካሄድ ቢጀምሩ የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ከመሆን ይልቅ ሥልጣናቸውን የሚጭኑ አምባገንን ገዢዎች በመንጋው ላይ ይሆናሉ። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የእግዚአብሔርን መንጋ እያጠሩ ያሉ እንደነዚህ ዓይነት መሪዎች በብዛት አሉ። መንፈሳዊ ስጦታዎችን በምንፈልግበት ወቀት ሊኖረን የሚገባ ብቸኛ ትክክለኛ ዓላማ እዚእብሔርንና ቤተ ክርስቲያንን በተሻለ መንገድ ማገልገል መሆን አለበት። እራሳችንን ሳይሆን ሌሎችን ለማነጽ መጣር ይገባናል። 

5. እግዚአብሔር አስፈላጊውን መንፈሳዊ ስጦታ ይሰጥህ ዘንድ በጸሎት ጠይቀው። እግዚአብሔር ጸሉትህን እንደመለሰ እድርገህ እስከምታምን ድረስ መጸለይህን ቀጥል። እግዚአብሔርን በጸሎት በምትጠይቀው ጊዜ፥ «እሺ» ወይም «እምቢ» የሚል መልስ ሊሰጥህ መብት እንዳለው አስታውስ። እግዚአብሐር ላሉት ጥያቄህ የሰጠው መልስ አይሆንም ከሆነ ሌላ የተሻለ ዕቅድ ለሕይወትህ ስላለው ብቻ ነው። 

6. ያንን መንፈሳዊ ስጦታ ላለው ሰው ሥልጣን እራስህን አስገዛ። ከእርሱ ወይም ከእርሷ ተማር። በእርሱ አመራር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማገልገል ጀምር። ያ ሰው እግዚአብሔር ይህን ስጦታ ሰጥተህ እንደሆነና እንዳልሆነ ሊያረጋግጥልህ ይችላል። 

ጥያቄ፡- ሀ) እጅግ አስፈላጊ መንፈሳዊ ስጦታዎች ተብለው ከላይ የተዘረዘሩትን መንፈሳዊ ስጦታዎች ተመልከት። በቤተ ክርስቲያናችሁ ውስጥ ከእነዚህ ስጦታዎች መካከል በጣም የሚፈለጉት ወይም የሌሉት ስጦታዎች የትኞቹ ይመስሉሃል? ላ) ከእነዚህ መንፈሳዊ ስጦታዎች እግዚአብሔር እንድትሳተፍባቸው የሚፈልገው የትኞቹ ይመስሉሃል? ከላይ የተመለከቱት ቅደም ተከተሎች እነዚህን ስጦታዎች ለመጠቀም እንድትጀምር እንዴት ይረዱሃል? 

መንፈሳዊ ስጦታዎቻችንን እንዴት እናውቃለን? 

ክፍሌ በማደግ ላይ ያለ ክርስቲያን ነበር። ክርስቲያን ከሆነ አንድ ዓመት ሆኖታል። ሌላ ክርስቲያን ደቀ መዝሙር እያደረገው ሲሆን ያለማቋረጥ ወደ ቤተ ክርስቲያን ይሄድ ነበር። ክፍሌ፥ እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዲሳተፍ እንደሚፈልግ ተገነዘበ። ወጣቶች በሙሉ በመዘመራን ቡድን ውስጥ መግባት ይፈልጉ ነበር። ከዚህ ውጭ ግን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለማገልገል ብዙ ዕድል ያለ አይመስልም ነበር። አንድ ቀን ክፍሌ ከሽማግሌዎች ወደ አንዱ በመሄድ «በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለመሥራት እፈልጋለሁ፤ ምን ማድረግ እችላለሁ?» በማለት ጠየቀ። 

ጥያቄ፡- ሀ) ሽማግሌ ብትሆን ኖሮ ለክፍሌ የምትሰጠው መልስ ምን ይሆን ነበር? ለ) በቤተ ክርስቲያን ምእመናንን ሁሉ በአገልግሎት እንዲሳተፉ ማድረግ ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው? ሒ እንድ የቤተ ክርስቲያን መሪ ምእመናኑ መንፈሳዊ ስጦታዎቻቸውን እንዲያውቁ [ለማድረእንዴት አብሮአቸው መሥራት ይችላል? መ) መንፈሳዊ ላጦታዎችህ የትኞቹ እንደሆኑ ታምናለህ? ሀ) መንፈሳዊ ስጦታዎች እዚያ እንደሆኑ እንዴት ታውቃለህ? 

ሰዎች ብዙ ጊዜ በሕይወታቸው ትግል ከሚገጥሙባቸው ጥያቄዎች አንዱ መንፈሳዊ ስጦታዎቻቸው የትኞቹ እንደሆኑ የመወሰን ጉዛይ ነው። ብዙ ክርስቲያኖች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከመሳተፍ የሚታቀቡት መንፈስ ቅዱስ የሰጣቸውን ስጦታዎች ባለማወቃቸው ነው። ሌሎች ከርሰቲያኖች ደግሞ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማምላክን ብቻ ይፈልጋሉ። ወደ ቤተ ክርስቲያን በመምጣት መዝሙር ይዘምራሉ። ደግሞም የእግዚአብሔርን ቃል ይሰማሉ። ነገር ግን በሌሎች ነገሮች ለመሳተፍ ፈቃደኛ አይደሉም። በሁለቱም መንገዶች ቢሆን መንፈስ ቅዱስ የሰጣቸው መንፈሳዊ ስጦታዎች አገልግሎት ላይ አልዋሉም። 

እንደዚህ ዓይነት አመለካከት ቢያንስ ሁለት አሉታዊ ውጤቶች አሉት፡- 

1 ግለሰቡ የበሰለ መንፈሳዊ ክርስቲያን ሆኖ ለማደግ አይችልም። ስኤፌ. 4፡12-13 የመንፈሳዊ ስጦታዎቻችን አጠቃቀም ከመንፈሳዊ እድገታችን ጋር በቅርብ የተያያዘ መሆኑን እናነባለን። መንፈሳዊ ስጦታችንን ካልተጠቀምን ራስ ወዳድ ወደ መሆን እናዘነብላለን። በራሳችን ዕቅድ ላይ ብቻ በማተኮር ሰዎችን በእምነታቸው ያድጉ ዘንድ እንዴት እንደምንረጻቸው ሳናስብ እንቀራለን። በኃላፊነት ከመሳተፍ ይልቅ በመገልገል ብቻ የምንረካ ከሆነ ባለመሳተፋችንና እግዚአብሔር የሰጠንን ስጦታዎች ባለመጠቀማችን . እምነታችን አያድግም። 

ጥያቄ፡– በቤተ ክርስቲያንህ ስላሉ አባላት አስብ። አብዛኛዎቹ መንፈሳዊ ስጦታዎቻቸውን በመጠቀም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይሳተፋሉን? ካልተሳተፉ ለምን? 

2. ቤተ ክርስቲያን መሆን ያለባትን ያህል ስኬታማ አትሆንም። ጳውሎስ ብዙ ጊዜ ቤተ ክርስቲያንን ከአካል ጋር እንደሚያወዳድር ትዝ ይልሃል። በክርስቶስ አካል ውስጥ ሰዎች የተለያዩ ክፍሎችን እንዲይዙ የሚያደርጉአቸው እነዚህ መንፈሳዊ ስጦታዎች ናቸው። ስለዚህ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሰዎች መንፈሳዊ ስጦታቸውን ካልተጠቀሙ አካሉ እንደታመመ ወይም ጎዶሎ እንደሆነ ያህል ነው። ለምሳሌ እዚእብሔር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ላሉ ሰዎች የወንገላዊነት ስጦታ እንደሰጠ እናስብ። ወንጌልን ወልዳኑ ሰዎች የሚያደርሱ ስለሆነ የቤተ ክርስቲያን «እግሮች» ናቸው እንበል። እዚህ ሰዎች ስጦታቸውን ተጠቅመው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ካልተሳተፉ ቤተ ክርስቲያን እግር አልባ እንደሆነች ይቆጠራል። ቤተ ክርስቲያን አካለ ጎዶሎ ሆነች ማለት ነው። 

ነገር ግን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሌላ ችግርም አለ። መንፈሳዊ ስጦታቸው ባልሆነ አገልግሎት ውስጥ የሚሳተፉ ብዙዎች አሉ። የማስተማር ስጦታ የሌላቸው ሰዎች በእሑድ ትምህርት ቤት ለማስተማር ይሞክራሉ። ወይም የወንጌላዊነት ስጦታ የሌላቸው ሰዎች በወንጌላዊነት ይመደባሉ። ይህ የሚሆነው ለምንድን ነው? 

1 አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ከዚህ ሥልጣን ጋር የሚመጣውን ክብር ስለሚፈልጉ ነው። በቤተ ክርስቲያን ያሉ ሰዎች ታዋቂ ወንጌላዊያን እንዲሉአቸው ይፈልጋሉ። ለራሳቸው ክብርንና ሥልጣንን በመፈለግ በትዕቢት ያገለግላሉ። እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ቤተ ክርስቲያንን ከመገንባት ይልቅ ያፈርሳሉ። 

2. አንዳንድ ጊዜ ይህ የሚሆነው ሰዎች በሌሎች ሰዎች አማካኝነትና በተሳሳቱ ምክንያቶች ወደ ሥልጣን (ኃላፊነት) ስፍራዎች ስለሚመጡ ነው። ለምሳሌ በአንድ ትምህርት ዲግሪ ያለው ሰው በትምህርቱ የተነሣ ብቻ የአስተማሪነት ስፍራ ይሰጠዋል። ትምህርቱ ከመንፈሳዊ ስጦታዎች ጋር ያለው ግንኙነት እጅግ አነስተኛ ነው። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ብዙ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ከሚገኝ ስጦታ ይልቅ ትምህርትን እናከብራለን። ወይም የአንድ ታዋቂ ወንጌላዊ ልጅ በመሆኑ አንድን ሰው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የአንድ ቢሮ ኃላፊነት እንሰጠዋለን። መንፈሳዊ ስጦታዎች በዘር የሚተላለፋ አይደሉም። 

ጥያቄ፡- እነዚህን ሁለት ችግሮች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያየኽው እንዴት ነው? 

ስለዚህ መንፈሳዊ ስጦታዎቻችንን የምናውቀው እንዴት ነው? ቀጥሎ በዚህ ጉዳይ አንዳንድ አሳቦች ተሰጥተዋል። 

1. በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ ተሳተፍ። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማገልገል የማትፈልግ ከሆነ እግዚአብሔር ስጦታህን ላማሳየት ይቸገራል። , በቤትህ ቁጭ የምትል ከሆነ ወይም በቤተ ክርስቲያን የሚካሄደው ነገር አንዳችም ግድ የማይሰጥህ ከሆነ ወይም ደግሞ እራስህን እጅግ ሥራ : የሚበዛበት ሰው አድርገህ የምትጥር ከሆነ መንፈስ ቅዱስ ስጦታህ ምን እንደሆነ ሳያሳይህ ዕድሜህ ያልፋል። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የምትሳተፍ ከሆነ ግን መንፈስ ቅዱስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዴት ማገልገል እንዳለብህ ያሳይሃል። 

አስታውስ መንፈሳዊ ስጦታዎች ጾታ ለይተው የሚሰጡ አይደሉም። እግዚአብሔር አንዳንድ ስጦታዎችን ለወንዶች ብቻ እንደሚሰጥ የሚያመለክት ነገር እናገኝም። ሆኖም ግን ከመንፈሳዊ ስጦታዎች አንዳንዶቹ , በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለወንዶች ብቻ ክፍት የሆኑና የሚቆጣጠሩአቸው ሊሆኑ ይችላሉ። ይህ ማለት ግን ሌቶች እነዚህ ለጦታዎች የሏቸውም “ሊጠቀሙባቸው የሚችሉበት መንገዶችም የሉም ማለት አይደለም። ለምሳሌ አዲስ ኪዳን ሌቶች በወንዶች ላይ ሥልጣን መያዝ እንደማይገባቸውና በጉባኤ ማስተማርም እንደሌለባቸው ያስጠነቅቃል። ሆኖም ግን በሌሎች ሁኔታዎች ሴቶች ማስተማር እንዳልተፈቀደላቸው የሚናገር አሳብ በአዲስ ኪዳን ፈጽሞ አናገኝም። ሌሎች ሴቶችን ወይም ልጆችን ማስተማር ይችላሉ። 

የተቻለህን ያህል በተላያዩ አገልግሎቶች ተሳተፍ። ማስተማር፥ መስበክ፥ ወንጌልን መመስክር፥ መምከር፥ መርዳት፥ ወዘተ… ሞክር። የተለያዩ አገልግሎቶች ውስጥ በተሳተፍክ ቁጥር መንፈሳዊ ስጦታዎችህ የትኞቹ እንደሆኑ የማወቅ ዕድልህ እየሰፋና እያደገ ይመጣል። 

መንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ ስጦታዎቻችንን ከእኛ ለመሰወር አይጥርም። በቤተ ክርስቲያን አጠቃላይ ሕይወት ውስጥ በተሳተፍን ቁጥር መንፈስ ቅዱስ የሰጠንን መንፈሳዊ ስጦታዎች መጠቀም እንችላለን። መንፈሳዊ ስጦታዎቻችንን ማወቅ ምሥጢራዊ ልምምድ አይደለም። ተፈጥሮአዊና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሠራን መጣን እየተረጋገጠልን የሚሄድ ነው። ውስጣዊ ዓላማችን ንጹሕ ከሆነና ቤተ ክርስቲያንን በትሕትና ካጎለጎልን መንፈስ ቅዱስ መንፈሳዊ ስጦታዎቻችን የትኞቹ እንደሆኑ ያሳየናል። 

ጥያቄ፡- ሀ) በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የምትሳተፍባቸውን ጉዳዮች በዝርዝር ጥቀስ። ለህ ደስ የምትሰኝባቸው አገልግሎቶች የትኞቹ ናቸው? ሐ) [አስቸጋሪ የሆኑብህ ነገሮች የትኞቹ ናቸው? መ) ከእነዚህ መካክላ መንፈስ ቅዱስ እንደሰጠህ የምታምነው የትኞቹን ነው? 

2. ደስ የምትሰኝባቸውና እግዚአብሔር እየባረከህ እንደሆነ የምታምንባቸውን አገልግሎቶች ፈልግ። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተሳትፎህ እያደገ በሄደ ቁጥር በሚገባ ውጤታማ እየሆንክ በምትሄድባቸው አገልግሎቶች ላይ ታዘነብላላህ። ምንም ፍሬ የማታፈራባቸው አንዳንድ አገልግሎቶች ይኖራሉ። እግዚአብሔር እጅግ በብዙ አንተን የሚባርክበት ሌሎች አገልግሎቶች ደግሞ ያጋጥምሃል። ይህ እግዚአብሔር በሆነ አካባቢ ስጦታ እንደሰጠህ የምትመለከትበት መንገድ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በአገልግሎት የምትሳተፈውም ስለተከፈለህ፥ ክብርን ስለምታገኝበት ወይም ሥልጣንን ስለሚያቀዳጅህ እንጻልሆነ ውስጣዊ ላማህ ንጹሕ መሆኑን ማረጋገጥ አለብህ። 

3. በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንድታደርግ የሚፈልገው ነገር ምን እንደሆነ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ለመጠየቅ በጸሎትህ በቂ ጊዜ ውሰድ፡፡ እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንድ አገልግሎት እንድትሰጥ የሰጠህ ልዩ ሸክም አለን? በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ክፍተት እንዳለ ያየኸው ልብህ የሚከብድበትና ያተኮርክበት አገልግሉት አለን? ይህ ከሆነ እግዚአብሔር በዚህ አገልግሎት ውስጥ እንድትሳተፍ ይፈልጋል ማለት ሊሆን ይችላል። እዚአብሔር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአንድ መንገድ እንድትሳተፍ ሊፈልግ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለአገልግሎቱ የሚሆን ስጦታ እንደሚሰጥህም እርግጠኛ መሆን ትችላለህ። በቤተ ክርስቲያን የሚጐድል ነገር መኖሩን በምትመለከትበት ወቅት ታላላቅ መንፈሳዊ ስጦታዎችን በትጋት የምትፈልበት አካባቢ ያ ሳይሆን አይቀርም። ስለዚህ እዚአብሔር በዚህ መንገድ እንዲጠቀምብህ ልትጠይቀው ይገባል። መንፈስ ቅዱስ ምን እንድታደርግ እንደሚፈልግ በሆነ መንገድ ያመለክትሃል። 

4. በሚገባ የሚያውቁህና እውነቱን ሊነግሩህ የሚፈቅዱ ክርስቲያን ጓደኞችህን መንፈሳዊ ስጦታህ ምን እንደሆነ ጠይቃቸው። ብዙ ጊዜ ለአንተ በቀላሉ የማይታዩ ነገሮችን ያያሉ። አንተ ልብ ባትላቸውም እንዳንድ ነገሮችን በሚገባ ስታከናውን አይተውህ ይሆናል። ለምሳሌ በአንዳንድ ሁኔታዎች ሌሎች ሊሰጡ የማይችሏቸውን የምክር አሳቦች የመስጠት ችሎታ ይኖርህ ይሆናል። ይህ የጥበብና የእውቀት ስጦታ እንደሆነ አንተ ሳትገነዘብ ሌሎች ይገነዘቡ ይሆናል። ስለዚህ በእነርሱ ምክር ይህን ስጦታ የበለጠ ልትጠቀምበትና ልታሳድገው ትችላለህ። ወይም አንተ ያለህበት እገላቀሉት የሚባርክ እንጸልሆነ በመናገር በዚያ አካባቢ ስጦታው ይኖርህ እንደሆነ ይጠይቁ ይሆናል። ለምሳሌ ብዙ ሰዎች የማስተማር መንፈሳዊ ስጦታ ሳይኖራቸው አስተማሪ ይሆናሉ። ተማሪዎቻቸው በሚገባ አይማሩም። የሚያስተምሩት ነገር አሰልቺ ይሆናል። ይህ መንፈሳዊ ስጦታቸው እንዳልሆነ ምልክት ነውና አገልግሎቱን ለሌሎች መተው አለባቸው። 

ብዙ ሰዎች መንፈሳዊ ስጦታዎችን የማወቅ ጉዳይ ቤተ ክርስቲያን ከምታስተምራቸው ትምህርቶች ሁሉ የላቀው እንዲሆን ይፈልጋሉ። መንፈሳዊ ስጦታዎቻችሁን ማወቅ እንተንም ሆነ ቤተ ክርስቲያንን የሚረዳ ቢሆንም እንኳ ዋናው ችግር ሰዎችን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ የማድረጉ ጉዳይ ነው። ብዙ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚሳተፉት ከአባላት 20% ብቻ ናቸው። 80% ቀን ወደ ቤተ ክርስቲያን በመምጣት መዝሙር ይዘምራሉ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ይሰማሉ፤ በዚህም ብቻ በመደሰት ይኖራሉ እንጂ በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በንቃት አይሳተፉም። ይህ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሽታ የመኖሩ ምልክት ነው። ሰዎች ሁሉ በአገልግሎት እንዲሳተፉ ማድረግ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ሁሉ ሚና ነው። የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ዋና ተግባር ምእመናን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስሙላት እንዲሳተፉ ማነጽ ነው። የአገልግሎት ዕድሎች ለሰዎች በሰፋ ቁጥር ሰዎችም ተሳትፎአቸውን ባሳደጉ መጠን መንፈስ ቅዱስ ወደሰጣቸው የአገልግሎት ስጦታ ማዘንበላቸው አይቀሬ ነው። ስለዚህ ሰዎች መንፈሳዊ ስጦታዎቻቸውን ያውቁ ዘንድ እንዲያጠኑ ከማድረግ ይልቅ ሰዎች በተላያዩ አገልግሎቶች ውስጥ እንዲሳተፉና ስጦታዎቻቸውን እጅግ በተላያዩ መንገዶች እንዲጠቀሙ በማድረግ ላይ ማተኮር ይገባል። አገልግሎት ሲሰጡ መከታተል፥ ፍርሃት በሚሰማቸው ጊዜ ማበረታታት ያስፈልጋል። መንፈሳዊ ስጦታዎቻቸውን ካወቅህ በኋላ ከፍተኛ ጥቅም ሊሰጥ በሚችልበት ሁኔታ ይጠቀሙበት ዘንድ እርዳቸው፥ አሳድግላቸው፥ ይጠቀሙበት ዘንድም እግዛቸው። 

ጥያቄ፡- ሀ) በቤተ ክርስቲያንህ ውስጥ ብዙ አባላት በአገልግሎት ያለመሳተፋቸውን ችግር የምታየው እንዴት ነው? ለ) የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ይህን ለመፍታት ምን እያደረጉ ነው? ሐ) የቤተ ክርስቲያን መሪዎች አንዳንድ አገልግሎቶቻቸውን ስጦታ ላላቸው ለሌሎች ሰዎች መልቀቅ አስቸጋሪ የሚሆንባቸው ለምንድን ነው? መ) በአመራር ላይ ያለውን የተሳሳተ አመለካከት ይህ እንዴት ያንጸባርቃል? 

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

%d bloggers like this: