የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በሰው ድነት (ደኅንነት) ውስጥ፤ ክፍል 1

ጥያቄ፡- ሀ) እንተ የመሰከርህለት ወይም ከሌላ ክርስቲያን የሰማኸው (የተአምራት ሁሉ ቁንጮ ምንድን ነው? ለ) ያንን ተአምራት ታላቅ ያደረገው ምን ነበር? 

በዙሪያችን ሁሉ አስደናቂ ተአምራትን እንሰማለን። ከእዚህ ተአምራት እንዳንዶቹ ሌሎች ክርስቲያኖች ሲናገሩ የሰማናቸው ናቸው። ሌሎቹን ደግሞ እራሳችን ስለተለማመድናቸው የምናያቸው ናቸው። ብዙ ጊዜ እነዚህ ተአምራት ከበሽታዎች መፈወስን ወይም ክከፉ መናፍስት ነህ መውጣትን የሚያካትቱ ናቸው ሰዎች ክሙታን እንደተነ እንኳ እንሰማለን። 

ይሁንና፡ ከሌሎች ተአምራት ሁሉ የላቀና ብዙ ጊዜ የሚሆን ሌላ ተአምር አለ። ምናልባትም ይህ ተአምር ከሁሉ አስደናቂ ነው። ይህ ተአምራት ምንድን ነው? የመንፈሳዊ ውልደት ተአምራት ነው። ድነት (ደኅንነት)ን በማግኘት የእግዚአብሔር ልጆች ስንሆን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በእውነት አስደናቂ የሆነ ተአምር ያደርጋል። መጽሐፍ ቅዱስ ከማመናችን በፊት በኃጢአታችን ምክንያት ሙታን እንደነበርን ይናገራል (ኤፌ. 2፡ህ። በድንገት ቀን ጊዜያዊ ሳይሆን ዘላለማዊ የሆነ መንፈሳዊ ሕይወት ተሰጠን ኈ(ዮሐ 3፡16)። ከዚህ ቅጽበት በኋላ የእግዚአብሔር ልጆች ሆንን (ዮሐ 1፡12)። ብዙ ክርስቲያኖች ሥጋዊ አካል ላይ የሚታይ ተአምር ለማየት ይናፍቃሉ። ይህን በማድረጋቸው ከሁሉ የላቀውን የድነት (ደኅንነት)ን ተአምር ይረሳሉ። 

በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የተገለጠውን የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በምናጠናበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ የተለያዩ አገልግሎቶች እንደነበሩት ተመልክተናል። ከእዚህ አንዳንዶቹ አስደናቂ መሆናቸውንም አይተናል። ወደፊት በልሳናት ከመናገር ጋር ስለ ተያያዘውና በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ አወዛጋቢ ስለሆነው ርእስ እንነጋገራለን። አሁን ግን የመንፈስ ቅዱስ ጥናታችንን አትኩሮት በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ላይ ማድረጉን እናበቃና አዲስ ኪዳን ስለ መንፈስ ቅዱስ የሚያስተምረውን ርእስ በርእስ እንመለከታለን። በዚህ ሳምንት ትምህርት፥ እኛን የእግዚአብሔር ልጆች ባደረገውና የተአምራት ሁሉ ቁንጮ በሆነው ተአምር ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ራሱ ስላለው ሚና እናጠናለን። 

ጥያቄ፡- ሀ) የእግዚአብሔር ልጅ የሆንከው እንዴት እንደሆነ በአጭሩ ግለጽ። ለ) ከተላማመድካቸው ሌሎች ተአምራት ሁሉ ይኸኛው ለአንተ በጣም አስፈላጊ የሆነው እንዴት ነው? 

ጥያቄ፡– የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብብ። ዮሐ 3፡3-7፤ 16፡8-11፤ ቲቶ 3፡5። መንፈስ ቅዱስ ይሠራል ስለሚባለው ሥራ ዘርዝር። ሥራው ስለሚያካትታቸው ጉዳዮች አጭር ማብራሪያ ጻፍ። 

አሐዱ ሥሉስ የሆነው አምላክ የደኅንነታችን ዋነኛ አከናዋኝ ነው። የእግዚአብሔር ልጆች ያደርጉን ዘንድ እያንዳንዱ የሥላሴ አካል ፍጹም በሆነ ስምምነትና አንድነት ይሠራሉ። ነገር ግን ያልዳነውንና በመንፈሱ ሙት የሆነውን ሰው ወደ አዲስ ፍጥረት በመቀየር እንደ እግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ መንገድ እንዲኖር የሚያስችላውና የኃያሉ እግዚአብሔር ማደሪያ የሚያደርገው ከሥላሴ አካላት አንዱ የሆነው መንፈስ ቅዱስ ነው። 

መንፈስ ቅዱስ በአንድ ሰው ሕይወት ሊሠራ፥ ከአነስተኛ ብልጭታ ተነሥቶ ይህ ነው የማይባል ኃይል እስከሚጎናጸፍ እያደር እንደሚያይል የባሕር ሞገድ ይመስላል። በዚህ አኳኋን ግላስቡ መንፈስ ቅዱስ በውስጡ አድሮ የክርስቶስ አንዱ ብልት እስከሚሆን ሥራውን በፀጥታና በእርጋታ ይጀምርና ወደ ከፍተኛ ደረጃ ያድጋል። በመጨረሻ ሰውዬው በኢየሱስ ክርስቶስ ሲያምን መንፈስ ቅዱስ ወደ ከፍተኛ የተግባር እንቅስቃሴ በመሸጋገር ታላቁንና የተአምራት ሁሉ ቁንጮ የሆነውን ተአምር ይፈጽማል። 

በቅድሚያ የምናጠናው በምድር ላይ ያሉ ሰዎችን በሙሉ በፀጥታና በማይታይ ሁኔታ የሚዳስሱትን ሁለት የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶችን ነው። የሥነ መለኮት ትምህርት አዋቂዎች ይህንን ሥራ «የአጠቃላይ ጸጋ» ሥራ ይሉታል። ይህ የእግዚአብሔር ልጆች ለሆኑትም ሆነ ላልሆኑት ሁሉ በረከት እንዲዳረስ መንፈስ ቅዱስ በምድር ሁሉ ላይ የሚሠራው አጠቃላይ ሥራ ነው። እግዚአብሔር ላጻድቃንና ለኃጥአን ዝናምን እንደሚያዘንብ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል (ማቴ. 5፡45)። ክርስቲያን ብንሆንም ባንሆንም ሕይወት በሙሉ የእግዚአብሔር አጠቃላይ ውጤት ነው። በብሉይ ኪዳን ላለነበረው አገልግሎት በትምህርት ሦስት ስናጠና የሁሉንም ሕይወት የሚጠብቀውና በምድር ላይ አዲስ ሕይወትንም የሚፈጥር መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ተመልክተናል። እዚህ ላይ ግን የምናተኩረው ከሰው ድነት (ደኅንነት) ጋር በሚያያዙት የአጠቃላይ ጸጋ ሁለት ገጽታዎች ላይ ይሆናል። 

1. የመንፈስ ቅዱስ ኃጢአትን የመከለል ሥራ (2ኛ ተሰ. 2፡5-12 አንብብ) 

በ1ኛና 2ኛ ተሰሎንቄ መጻሕፍት ጳውሎስ በመጨረሻዎቹ ቀናት የሚገለጡ እውነቶችን ያስተምራል። በትምህርቱ መካከል ላይ ስላ ዓመፅ ሰውና እርሱን ስለሚከላከለው ይነግረናል። ይህ ክፍል ለመረዳት አስቸጋሪ የሆነ ሲሆን ሊቃውንትም በአተረጓጐም ይላያዩበታል። ቢሆንም ከሁሉም የቀረበው አተረጓጐም የሚከተለው ነው። 

ሀ. የዓመፅ ሰው በዚህ ክፍል ውስጥ ጳውሉላ የሚነግረን በዚህ ዓለም የሚሠራ የዓመፅ መንፈስ እንዳለ ነው። ይህ ዓመፅ በተለያዩ መንገዶች እግዚአብሐርን አለመታዘዝን ያስከትላል። አንድ ቀን ይህ ልዩ የሆነ የዓመፅ ሰው እንደሚገለጥ ጳውሉዕ ይናገራል። እርሱም በሰው ልጅ ውስጥ ያለው ክፋት ሁሉ እለስ «ገለጥ የሚሠራ ይሆናል። የሒትለር፥ የስታሊንና የመንግሥቱን ክፋት በአንድ ላይ አጠቃልሎ የያዘ ሰውን የሚመስል ይሆናል። ኃይሉን የሚያገኘው ከሰይጣን ነው። ከኃይሉ ታላቅነት የተነሣ 

ብዙ ዓይነት ተአምራቶችን ያደርጋል። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ከእውነት ወደ ክፋት ይመራቶዋል። ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግም ሊመጣ ን ሙሉ በሙሉ ድል ያደርገዋል። ጳውሎስ በዚህ ቦታ የሚገልጸውን፥ ዳንኤል፥ «ትንሹ ቀንድ። (ዳን 7፡8) ከላውና በራእይ መጽሐፍ ደግሞ «አውሬው» ከተባለው (ራእይ 17፡8) ጋር ስናወዳድረው ሁሉም የሚናገሩት ስለ አንድ ሰው ይመስላል። ሁሉም የሚገልጹት ዓለምን በእግዚአብሔርና በቅዱሳኑ ላይ ለመጨረሻ ጊዜ የሚያስከትተውን የመጨረሻውን የዓለም ገዢ ሐሰተኛው ክርስቶስን ነው (1ኛ ዮሐ 2፡1፥ 18)። 

ለ. የዓመፅ ሰውን ከልካይ፡- ይህ ክፉ ሰው ወደ ለም መድረክ እንዳይመጣ የሚከለክለው ምንድን ነው? ጳውሎስ እንደሚናገረው እንዳይገለጥ ያገደውና የሚከላከለው አለ። ይህ ከልካይ ማን እንደሆነ የተለያዩ አሳቦች ይሰጣሉ። አንዳንዶች የሮም መንግሥት ነው ብለው ያስባሉ። ሌሎች ደግሞ ከመጨረሻው ዘመን በፊት ከዓለም የምትወሰደው ዓለም አቀፍዋ ቤተ ክርስቲያን ናት ይላሉ (1ኛ ተሰ. 4፡13-18)። ሌሎች ደግሞ እስካሁን ድረስ በብዙ መንግሥታት ውስጥ በሚገኙት ሕግና ሥርዓት ላይ ያለው እምነት ነው ይላሉ ነገር ግን በጣም የሚያሳምነው አገላለጽ የሚከተለው ነው። ይኸውም፡ ‹የሚከለክል› የሚለው ቃል የሚያመለክተው በዓለም የሰፈነው አጠቃላይ ኃጢአት እንዲወገድ የመንፈስ ቅዱስ ህልውናና ሥራ ላላሚያከናውኑት የመከልከል ተግባር ነው። ሐሰተኛ ክርስቶስ ተገልጦ ምድርን በቁጥጥሩ ሥር ከማስገባቱ በፊት መደረግ ያለበት ነገር አለ። ይኸውም በሰው ልብ ውስጥ ያለው ክፋት ያለገደብ ተላቅቆ በምድር ላይ ጥፋት እንዳይስፋፋ የሚከለክለው የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት ይገታል። . . ከዚያም እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ከምድር ላይ ይወለደዋል። በዚያን ጊዜ ታላቅ ክፋት በምድር ላይ ይገለጣል። ይህ ክፋት የሚቆመው ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልሶ መጥቶ በሙሉ ሥልጣን በሚገዛበት ወቅት ብቻ ነው። 

በዘፍ. 6፡3 እግዚአብሔር ስለ ኖህ ዘመን ክፋት ሲናገር «መንፈሴ በሰው ላይ ለዘላለም አይኖርም፥ እርሱ ሥጋ ነውና» ብሏል። ይህ የሚያሳየው ከኖህ ዘመን በፊት መንፈስ ቅዱስ የኃጢአትን መስፋፋት ለመከላከል ይሠራ እንደነበር ነው። መንፈስ ቅዱስ ኃጢአትን ይከላካል ካነበረበት መንገድ አንዱ የሰው ልጅ ሊሠራ የሚችለው ክፋት ሁሉ በምድር ላይ እንዳይታይ ዕድሜን መገደብ ነበር። «እግዚአብሔርም የሰው ክፋት በምድር ላይ እንደ በዛ፥ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደ ሆነ አየ» ተብሎ ስለዚያ ጊዜ ተጽፋል። ክፋት ምድርን የሞላ ቢሆንም እንኳ መንፈስ ቅዱስ የክፋትን ተግባራዊነት ይቆጣጠር ነበር። ክፋት ራሱን የሚያጠፋ ስለሆነ በጊዜው እግዚአብሔር ባይቆጣጠረው ኖሮ ሰውን ሁሉ ባጠፋ ነበር። ኖኅና ቤተሰቡ ብቻ ሲቀሩ የሰው ልጅ ሁሉ በጥፋት ውኃ እስኪጠፋ መንፈስ ቅዱስ በዚያ ዘመን የሰዎችን ክፋት ይቆጣጠር ነበር። 

አንዳንድ ሊቃውንት «የሚከለክላው» መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ የሚያስቡት ለምንድን ነው? በርካታ ምክንያቶች አሉ። 

1. በ2ኛ ተሰ. 2፡7 በግሪኩ ትርጉም ‹የሚከላክለው› ለሚለው ቃል የተሰጠው ተውላጠ ስም ለሰው የሚያገለግለው «እርሱ» የሚል ቃል እንጂ ለነገር ወይም ለዕቃ የሚያገለግል አቻ ቃል አይደለም። ይህ የሚያመለክተው ከልካዩ እንደ መንግሥት፥ ሕግ ወይም ቤተ ክርስቲያን ያለ ድርጅት ሳይሆን ሰብአዊ አካል መሆኑን ነው። 

2. ይህ ከልካይ ሰይጣን የዓመፅ ሰውን የእግዚአብሔር ትክክለኛ ጊዜ ከመድረሱ በፊት እንዳይልክ የመከልከል ኃይል ስላለው ከሰይጣን የላቀ ኃይል ያለው መሆን አለበት። ከሰይጣን የላቀ ኃይል ያለው እግዚአብሔር ብቻ ነው። ስለዚህ ከልካዩ እግዚአብሔር እራሱ እንደሆነ ይመስላል። 

3. ከልካዩን የተሰሎንቄ ክርስቲያኖች በሚገባ ያውቁት ነበር (2ኛ ተሰ. 2፡6)። ይህ ፈጽሞ በመጨረሻ ዘመን ለሚኖር ሰው የተነገረ ሊሆን አይችልም። 

እዚህ የምንማረው ነገር የሰው ልጅ በገዛ ክፋቱ እራሱን ከማጥፋት እንዲታቀብ መንፈስ ቅዱስ ክፋት እንዳይስፋፋና እጅግ አይሎ የእግዚአብሔርን ፍጥረታት ሁሉ እንዳይደመስስ በዓለም ውስጥ እንደሚሠራ ነው። መንፈስ ቅዱስ ክፋትን ለመከላከል መንግሥታትንና ሕግን ይጠቀማል። በምድር ላይ እንደ ጨውና ብርሃን የሆኑትን ክርስቲያኖችንም ይጠቀማል (ማቴ. 5፡13)። ሆኖም ግን አንድ ቀን የመንፈስ ቅዱስ የመከላከል ሥራ ያበቃል። አንዳንድ ክርስቲያኖች ይህ የመንፈስ ቅዱስ የመከላከል ሥራ ማብቃት ቤተ ክርስቲያን ክምድር ወደ ሰማይ ከምትወስድበት ጊዜ ጋር ይገጣጠማል። እናም በዚያን ጊዜ ሐሰተኛ ክርስቶስ ከመጨረሻው የክፋት መንግሥቱ ጋር በመገለጥ ዓለምን ይቆጣጠራል በማለት ያስተምራሉ። በዚያኑ ወቅት እግዚአብሔር ስዓላም ላይ ተፈጥሮአዊና ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ ፍርዱን መላክ ይጀምራል። ይህ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ንጉሥ በመገለጥ መንግሥቱን የሚያቋቁምበትን ሁኔታ የሚያመቻች ዝግጅት ነው። 

ጥያቄ፡- ሀ) የሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ያለ ክፋት እራሱን ለጥፋት ኃይል እንዳለው ሊያስረዱ የሚችሉ በዓለም የሚፈጸሙ ክስተቶችን ግለጽ። ለ) እግዚአብሔር የኃጢአት ኃይል በሙላት እንዳይገለጥ የሚከላከልባቸውን መንገዶች ግለጽ። 

2. በዓለም ያሉ ሰዎች ኃጢአተኛ መሆናቸውንና ድነት (ደኅንነት) እንደሚያስፈልጋቸው እንዲያውቁ የሚያደርግ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ( ዮሐ 16፡8-10። (በትምህርት 4 በዚህ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ላይ የተነጋገርነውን ከልስ) 

ሁለተኛው የጋራ ጸጋ አገልግሎት መንፈስ ቅዱስ በሰዎች ሁሉ ላይ የሚያደርገው ኃጢአትን የመውቀስ ተግባር ነው። ከመንፈስ ቅዱስ አጠቃላይ አገልግሎቶች አንዱ፥ አንድ ሰው ለድነት (ደኅንነት) ክርስቶስን ከመቀበሉ በፊት የሚፈጸመው ለምን ስለ ኃጢአት፥ ስለ ጽድቅና ስለ ፍርድ የመውቀስ አገልግሎቱ ነው። ይህ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ሁለት ውጤቶች አሉት። የመጀመሪያው የሰው ልጅ በሙሉ ምክንያት እንዲያጣ ማድረግ ነው። በተላያየ ደረጃ ይሁን እንጂ በአንድ ወይም በሌላ መንገድ መንፈስ ቅዱስ በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ በመሥራት ኃጢአተኞች መሆናቸውንና በእግዚአብሔር ላይ በማመፅ እንደሚኖሩ ያስረዳል። ስለ ኢየሱስና በመስቀል ላይ ስለ መሞቱ ያልሰሙ ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በሕይወታቸው በመሥራት በእግዚአብሔር ላይ ስለሚፈጽሙት ኃጢአት ይወቅሳቶዋል። የሰው ልጆች በሙሉ በእግዚአብሔር ፊት ላፍርድ ሲቀው እግዚእብሔር ከሚጠቅሳቸው ነገሮች አንዱ ባስተማራቸው እውነት ላይ ሰላማመፃቸው ነው። ይህም ሰዎችን ምክንያትአልባና ለዘላለም ቅጣት የተገቡ ያደርጋቸዋል። እነዚህ ሰዎች ኃጢአተኞች መሆናቸውንና እግዚአብሔር ያዘጋጀውን የጽድቅ መንገድ መቀበል እንደሚገባቸው መንፈስ ቅዱስ በሚነግራቸው ወቅት ለማድመጥ አሻፈረኝ ያሉ ናቸው። (እግዚአብሔር ስለ ራሱ የሚያስተምርበትን አጣቃላይ ጸጋ ሰዎች ከመቀበል እንዴት እምቢ እንደሚሉ በበለጠ ለመረዳት ሮሜ 1፡18-32 ተመልከት)። 

በሁለተኛ ደረጃ መንፈስ ቅዱስ ሰዎች ከኃጢአታቸው በመመለስ ድነት (ደኅንነት)ን ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ ያደርጋል። ሰዎች በእግዚአብሔር የሚፈረድባቸው ኃጢአተኞች መሆናቸውን፥ በኢየሱስ በማመን ጻድቅ ሊሆኑ እንደሚችሉ ካልተረዱ በስተቀር ለደኅንነታቸው እግዚአብሔርን ሊፈልጉት አይችሉም። ስለዚህ አንድ ሰው ክርስቲያን ከመሆኑ በፊት መንፈስ ቅዱስ በሕይወቱ ከሚሠራቸው ሥራዎች ትልቁ ስላ ኃጢአት በሚገባ እንዲያውቅና ለድነት (ደኅንነት) ወደ ክርስቶስ እንዲመለስ ማድረግ ነው። መንፈስ ቅዱስ ማንም ሰው ክርስቲያን እንዲሆን እያስገድድም። እግዚአብሔር ሁልጊዜ የመምረጥ መብታችንን ይጠብቃል። መንፈስ ቅዱስ ግን መንፈሳዊ ጆሮዎቻችንና ዓይኖቻችን እንዲክፈቱና እውነትን አውቀን ያንን እውቀት ለመቀበል ወይም ላለመቀበል እንድንወስን ይፈልጋል። 

ጥያቄ፡- አማኝ ከመሆንህ በፊት መንፈስ ቅዱስ በሕይወትህ ሠርቶአል ብለህ የምታስባቸውን መንገዶች ግለጥ። 

3. ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያምን ለማዘጋጀት ታላቁ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ (ዮሐ 3፡3-7፤ ቲቶ 3፡5)። 

ይኸውም ሰው ወደ ክርስቶስ ሲመለስ የሚፈጸመውን ክተአምራት ሁሉ የላቀውን ተአምር ማድረግ ከዚያም በፊት እንዲያምን ማዘጋጀት ሁለቱ የመጀመሪያዎቹ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች ናቸው። ይህ ተአምር በአብዛኛው በስውር የሚከናወን ስለሆነ እንደ አስደናቂ ተአምር አንቆጥረውም። ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ሰው ከመዳኑ በፊት እና ከዳነ በኋላ ስለሚገኝበት ሁኔታ የሚያስተምረውን ብንረዳ በእርግጥኛ ይህ ተአምር ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ እንገነዘባለን። 

በአዲስ ኪዳን ውስጥ ይህን የመንፈስ ቅዱስ ሥራ በሚያንፀባርቅ ሁኔታ ስለ ሰው ድነት (ደኅንነት) ምንነት የሚናገሩ በርካታ የተለያዩ ክፍሎች አሉ። እንዳንድ ጊዜ «አዲስ ልደት» ወይም «ሁለተኛ ዳግም ውልደት» ይባላል (ዮሐ 3፡3፥ 7፤ 1ኛ ዮሐ 3፡9-10)። ይሁን እንጂ መንፈስ ቅዱስ አንድ ሰው በሚድንበት ጊዜ በሰውዩው ልብ ውስጥ የሚሠራውን ሥራ ከሁሉም በላቀ ሁኔታ ለመግለጽ አዲስ የሕይወት እስትንፋስን መዝራት» ተብሎ ሲቀርብ የሰላጣ ይብራራል (ቲቶ 3፡5)። 

ብዙ ጊዜ ክርስቲያን ስለሆንባቸው ወቅቶች ስናስብ ትኩረት የምናደርገው በእኛ በኩል ስለ ተደረገው ነገር ነው። ንስሐ ገብተን በኢየሱስ በማመናችን እንደጻንን እንናገራለን። ተለወጥን እንላለን። ነገር ግን እነዚህ አባባሎች ትክክል ናቸውን? ያዳነን እምነታችን ነውን? ወይስ እምነታችን መንፈስ ቅዱስ ላደረገው ነገር ውጫዊ ማረጋገጫ ብቻ ነው? እምነት የድነት (ደኅንነት) 

መንገድ እንጂ ድነት (ደኅንነት)ን እንደማይሰጠን መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል። ድነት (ደኅንነት) መንፈስ ቅዱስ በሰው ልብ ውስጥ የሚያደርገው ታላቅ ተአምር ነው። እኛ የምናደርገው ድርጊት ውጤት አይደለም። በምንድንበት ወቅት መንፈስ ቅዱስ ምን እንደሚያደርግ ለመረዳት ክመጻናችን በፊት የነበረንና በኋላ የሚኖረንን ሁኔታ መመልከት ያስፈልገናል። ከመዳናችን በፊት በእርግጥ ምን እንመስል ነበር? ከዳንስ በኋላ ምን ሆነናል? 

ሀ. ከመዳናችን በፊት ምን እንመስል እንደ ነበር መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረን የሚከተለውን ነው። 

ጥያቄ፡- የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት። ኢሳ 59፡2፤ ዮሐ. 8፡44፤ ሮሜ 1፡18፤ 5፡10፤ 8፡7-8፤ 1ኛ ቆሮ. 2፡14፤ ኤፌ. 2፡1-3፤ 5፡8፤ ፊልጵ. 3፡18-19፤ 1ኛ ዮሐ. 3፡7-9። እነዚህ ጥቅሶች ከመዳናችን በፊት ስለነበርንበት ሁኔታ የሚያሳዩን ምንድን ነው? 

1. በመንፈሳችን ሙታን ነበርን፡- የሞተ ነገር በውስጡ ሕይወት የለውም። ለማሰብ፥ ለማቀድና፥ ለመምረጥ ችሎታ የለውም። ምንም ነገር ለማድረግ አይችልም። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈሳችን ሙታን ነበረን ሲል ክርስቶስ የሌላቸው በሙሉ በራሳቸው ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት ለማድረግ፥ መንፈሳዊ ነገሮችን ለማወቅና ለመረዳት ብሎም ለድነት (ደኅንነት) የራሳቸውን ምርግ ለማድረግ ምንም ችሉታ እንደሌላቸው ማመልከቱ ነው። ከእነዚህ የትኞዎቹም ከመሆናቸውም በፊት ሕይወትን የመስጠት ሂደት 

መጀመር አለበት። 

2. መንፈሳዊ ነገሮችን ለመረዳት የማንችል ነበርን፡- ዐሥጋም ሆነ በመንፈስ ለመዳን አንድ ሰው ያለበትን ሁኔታና የሚድንበትን መንገድ ማወቅ አለበት። ሙት ከሆነ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? ያልዳነ ሰው መንፈሳዊ ነገሮችን ለመረዳት ካልቻለ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? ለመታዘዝም ሆነ ላለመታዘዝ ምርጫ ለማድረግ እንኳ መንፈሳዊ ጆሮዎቹና ዓይኖቹ መከፈት አለባቸው። እርሱ በሰው ሕይወት ውስጥ አንድ ነገር እሲከሚያደርግ ድረስ ድነት (ደኅንነት) እንደሚያስፈልገንና የእግዚአብሔርን የድነት (ደኅንነት) መንገድ ላመረዳት ከሰብአዊ ችሎታ በላይ ነው። 

3. የኃጢአት ባሪያዎች ነበርን፡- ባሪያ የሆነ ሰው ሕይወቱን ሊቆጣጠር አይችልም። ዕቅዶቹ፥ አሳቦቹና ፍላጎቶቹ በሙሉ በአንድ ሌላ ኃይል ቁጥጥር ሥር ናቸው። ከመዳናችን በፊት የኃጢአት ባሪያዎች እንደ ነበርንና ኃጢአትም ይቆጣጠረን እንደነበር ተጽፏል። ኃጢአታችንን የማሸነፍ ችሎታ አልነበረንም። ኃጢአት ለማድረግ ባንፈልግም እንኳ ኃጢአት ይቆጣጠረንና እንድንፈጽመው ያስገድደን ነበር። ለኃጢአት ባሪያ የሆነ ሰው መልካም ለመሥራት ወይም መልካም መንገድን ይህም ማለት የእግዚአብሔርን መንገድ ለመከተል ምርጫ የለውም። 

4 በጨለማ ውስጥ ነበርን፡- ምንም ብርሃን በሌለበት ለማየት ፈጽሞ አይቻልም። እጅግ ጨለማ በሆነበት ሌሊት እንኳ ጥቂት ለማየት የሚረዱን ከዋክብት አሉ። ጭላንጭል ብርሃናቸው ከጠፋ ግን ምንም ነገር ማየት እስከሚሳነን ፍጹሙ ጨለማ ይከድነናል። ከመዳናችን በፊት በመንፈሳዊ ጉዳይ በፍጹም ጨለማ ውስጥ ነበርን። መንፈሳዊ የሆነ ምንም ነገር ለማየት አንችልም ነበር። ከነበርንበት ከጥልቁ ለመውጣትና ድነት (ደኅንነት)ን ለማግኘት እንድንችል የሚረዳን አንዳችም ብርሃን አልነበረም። 

5. በሰይጣን መንግሥት ውስጥ ነበርን፡- በአንድ መንግሥት ግዛት ሥር ያለ ሰው ሙሉ በሙሉ በዚያ መንግሥት ቁጥጥር ሥር ነው። ከመታዘዝና ከመገዛት በስተቀር ለማመፅ እንኳ አይችልም። ከመዳናችን በፊት ሙሉ በሙሉ በሰይጣን ቁጥጥር ሥር ነበርን። ፈቃዳችንን እንደ ፈቃዱ ይነዳ ስለነበር ምንም ማድረግ እንችልም ነበር። ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠርን ስለነበር ዓመፅ አካሂደን የእግዚአብሔር መንግሥት አካል ለመሆን ብንፈልግ እንኳ አንችልም ነበር። 

6. የእግዚአብሔር ቁጣ በላያችን ነበር፡- እግዚአብሔርንና ሕግጋቱን በመታዘዝ ለመኖር ፈቃደኞች ስላልሆንን የእግዚአብሔር የጽድቅ ቁጣ በላያችን ላይ ሆኖ ሁልጊዜ በእግዚአብሔር ፍርድ ሥር እንኖር ነበር። 

7. የእግዚአብሔር ጠላቶች ነበርን፡- በኃጢአት ተፈጥሮአችን ምክንያት ዘውትር የምናደርገው እግዚአብሔር ከሚፈልጋቸው ነገሮች ተቃራኒ የሆኑትን ነበር። እግዚአብሔር እንድናደርግ የከለከለንን ነገር በማድረግ እየኖርን ሌሎችም ይኽንኑ እንዲያደርጉት ልናበረታታ ነበርን። 

ጥያቄ፡- ሀ) ይህ ነገር ብዙ ሰዎች በኢየሱስ ለምን እንደማያምኑ ለመረዳት እንዴት ያግዘናል? ለ) ይህ ነገር ከመዳናችን በፊት አንድ ተአምር መፈጸም እንዳለበት እንዴት ያስረዳናል? ሐ) ከጨለማ አምልጠህ በብርሃን ለመወመላለስ የረዳህን እግዚአብሔርን ስለ ምሕረቱና ጻጋው ለማመስገን ጊዜ ውሰድ። 

ለ. መንፈስ ቅዱስ እኛን የሚያድንበት ሂደት 

መጽሐፍ ቅዱስ ከክርስቶስ ውጭ ስላለ ሰው የሚያሳየን ሥዕል በጣም የዉለወ ነው። የድነት (ደኅንነት)ን መንገድ ለመምረጥ ምንም መላ የለውም። እግዚአብሔርን በመምረጣችን አንዳንዶቻችን ትምክህት የሚሰማን ከማመናችን በፊት የነበረንን ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ለለማንረዳ ነው። የነበርንበት ሁኔታ አስከፊነትና በኢየሱስ ማመን ፈጽሞ ያለመቻላችንን ከተረዳን በኢየሱስ ማመን እንድንችል መንፈስ ቅዱስ የሠራው ተአምር ምን ያህል ገናና እንደሆነ እንገነዘባለን። እግዚአብሔር አብ፥ እግዚአብሔር ወልድና እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጆች ያደርጉን ዘንድ የሠሩትን ታላቅ ሥራ የምንረዳው ተስፋ-ቢስ የነበርን መሆናችንን በሚገባ ስንገነዘብ ነው። ታላቅ ምሕረቱንና ጸጋውን፥ እንዲሁም በጸጋው ብርሃን ዛሬ ሐሌት የምናደርግባቸውን ብዙ በረከቶች የምናስተውለው ያኔ ብቻ ነው። 

ጥያቄ፡– ሮሜ 8፡28-30 አንብብ። እነዚህ ጥቅሶች በደኅንነታችን ሂደት ውስጥ እግዚአብሔር ስለሚሠራው ታላቅ ሥራ ምን ያስተምሩናል? 

መጽሐፍ ቅዱስ የሰው ድነት (ደኅንነት) ሂደት እንደሆነ ያስተምረናል። በዚህ ሂደት ትልቅ ሚና የሚናወተው መንፈስ ቅዱስ ነው። የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ፈንታ ከመቆሙ የተነሣ አማኝ ሆነን በተቀዳጀነው ዋስትና ላይ ጳውሎላ ያለውን ትኩረት ለመግለጽ በርካታ ቃላትን በመጠቀም ያብራራዋል። ሮሜ 8፡28-30 የድነት (ደኅንነት)ን ሂደት ከእግዚአብሔር አመለካከት አኳያ ያሳየናል። ሰው ይድን ዘንድ እግዚአብሔር በሕይወቱ ምን እንደሚያደርግ ይተነትናል። ትኩረቱ በድነት (ደኅንነት) ሂደት ውስጥ ሰው በሚሰጠው ምላሽ ላይ አይደለም። እግዚአብሔር ከእያንዳንዳችን ጋር ያለው ግንኙነት የጀመረው «በቅድመ-እውቀቱ» ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይህ ሐረግ የሚያመላክተው እግዚአብሔር እንደምንድን አስቀድሞ ማወቁን ብቻ ሳይሆን በሉዓላዊ በጎነቱ ከእኛ ጋር ኅብረት ለመፍጠር አስቀድሞ የወሰነ መሆኑን ጭምር ነው። ጳውሎስ አስቀድሞ ያውቃቸውን «ወሰናቸው» ይላል። እግዚአብሔር፡ አስቀድሞ የወሰነው ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖረው ብቻ ሳይሆን ኢየሱስ ክርስቶስን እንድንመስል እንደሚያደርገንም ጭምር ነው። እግዚአብሔር አስቀድሞ ልጆቹ ይሆኑ ዘንድ የወሰናቸውን ጠራቸው። በዚህ ቦታ ባይገለጥም እንኳ እንድናምን ይህ ጥሪ ወደልባችን የመጣው በመንፈስ ቅዱስ ስኩል ለመሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም። የመንፈስ ቅዱስን ጥሪ የተቀበሉትን እግዚአብሔር ያጸድቃቸዋል። ይህ ማለት በደለኞች አይደሉም በማለት ስለ እኛ ይመሰክራል፥ ደግሞም በክርስቶስ ኢየሱስ ውስጥ እንደ ንጹሐን ይመለከተናል ማለት ነው። የሂደቱ ማጠቃለያ እግዚአብሔር እንደሚያከብረን የሰጠን ተስፋ ነው። ወደ መንግሥተ ሰማይ ሊወስደን እንደ እግዚአብሔር ልጆች የሚጠብቀንን ክብር ሊያጎናጽፈን ቃል ይገባል። እንዴት ዓይነት አስደናቂ ሂደት! እንዴት ዓይነትስ አስደናቂ አምላክ ነው። 

ሐ. ከዳንን በኋላ ምን እንደምንመስል የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት 

ጥያቄ፡– የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብብ። ዮሐ 1፡12፤ 5፡24፤ ኤፌ. 2፡4-10፤ ቈላ. 1፡13፥ 19-22፥ 27፤ 2፡13-14፤ 2ኛ ቆሮ. 5፡17፥ 21። እነዚህ ጥቅሶች አንዴ ከዳንን በምንኖረው ሕይወት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ስለሚፈጥረው ልዩነት ምን ያስተምሩናል? 

መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን የሚሠራው ተአምራት እጅግ ታላቅ ከመሆኑ የተነሣ ሁለንተናችንን ይለወጣል። በፊት ሙታን ነበርን፥ አሁን ግን ሕያው ነን። መንፈሳዊ ነገሮችን ለመረዳት አንችልም ነበር፥ አሁን ግን እንችላለን። በአንድ ወቅት የኃጢአት ባሪያዎች ነበርን፥ አሁን ግን በክርስቶስ ነፃነት አላን። ቀድሞ ስጨላማ ነበርን፥ አሁን ግን በብርሃን እንኖራለን። ቀድሞ በሰይጣን ግዛት ውስጥ ነበርን፥ አሁን በኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥት ውስጥ ነን። ኃጢአታችን ሙሉ በሙሉ ይቅር ተብሏል። አሁን ጻድቅ፥ አዲስ ፍጥረት የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ዘላለማዊ ሕይወትም አለን ወዘተ…። 

ጥያቄ፡- ሀ) አንድን ሰው በአካል ከሞት እንዲነግ ከማድረግ ይልቅ ይህ ከፍተኛ ለውጥ ታላቅ ተአምር የሚሆነው እንዴት ነው? ለ) ለእግዚአብሔር ይህን ተአምራቶች በሕይወትህ ስላደረገ ጊዜ ወስደህ  አመስግነው። 

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.