የመንፈስ ቅዱስ ስሞች

ጥያቄ፡- ምሳ. 810 «የእግዚአብሔር ስም የጸና ምብ ነው ጻድቅ ወደ እርሱ ሮጦ ከፍ ከፍ ይላል፡- ሀ) የእግዚአብሔር ስም ለእግዚአብሔር ሕዝብ መሸሸጊያ የሚሆነው በምን መንገድ ነው? ለ) የጌታን ስምና ትርጉሙንም ማወቅ እንዴት እንደሚያበረታታህ ዓለጽ? ሐ) ከአበረታቱህ የእዚአብሐር ስሞች አንዳንዶቹን ጥቀስ። 

ትናንትና ባካሄድነው የቃለ ምልልስ ሥራ ስለ እግዚአብሔርና ስለ መንፈስ ቅዱስ በጠየቅሃቸው ጥያቄዎች እጅግ የተለያዩ መልሶች እንዳገኘህ እንገምታለን። ለለ መንፈስ ቅዱስ ጉዳይ በክርስቲያኖች መካከል ተራ የሚያጋቡ በርካታ አሳቦች አሉ። ይህ ራ መጋባት የተፈጠረው ለምንድን ነው? ለዚህ ተቀዳሚው ምክንያት ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚያስተምርና እነዚህን ጥያቄዎች እንዴት እንደሚመልስ ለማወቅ ጊዜ ስለማይሰጡ ነው። የዚህ ስለ መንፈስ ቅዱስ የተጻፈ የጥናት መጽሐፍ ተቀዳሚ ዓላማ መጽሐፍ ቅዱስን በመቃኘት ለእነዚህና ሌሎች ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ነው። 

ጥያቄ፡- ሀ) ወመንፈስ ቅዱስ «ቅዱስ መንፈስ» ተብሎ የተጠራበት ምክንያት ምንድን ነው ብለህ ታስባለህ? ለ) ቅዱስ ማለት ምን ማለት ነው? ሐ) መንፈስ ማለት ምን ማለት ነው? መ) የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት። ዘፍ 2 ማቴ. 3፡16 የሐዋ. 16፡7፤ ሮሜ 8፡9፤ ራእ. 14። የመንፈስ ቅዱስን ሌሎች ስሞች ጥቀስ። 

ብዙ ጊዜ የእግዚአብሔርን ስም ዝም ብለን ከመጥራትና ከመጠቀም በስተቀር ምን ማለት እንደሆነና እግዚአብሔር በዚያ ስም ለሦን እራሱን እንደገለጠልን ቆም ብለን አናስብም። የእግዚአብሔር ስሞች በተቀዳሚ ባሕርይውን ለመመለጥ የተሰጡ ናቸው። ለምሳሌ እግዚአብሔር አብ «አባት» ተብሎ የተጠራው በኢየሱስ ክርስቶስ ላመኑ ለልጆቹ ያለውን የፍቅር እመለካከት ለማሳየት ነው። «ኢየሱስ» ማለት ድነት (ድነት (ደኅንነት)) ማለት ሲሆን በመስቀል ላይ በመሞት ድነት (ድነት (ደኅንነት))ን ለሰው ልጆች መስጠት ተቀዳሚ ተግባሩ ሆኑን ያሳያል። «መንፈስ ቅዱስ» የሚለው ስም ለሦስተኛው የሥላሴ አካል የተሰጠበት ምክንያት ደግሞ አለ። 

ጥያቄ፡- «መንፈስ» የሚለውን ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ላይ ተመልከት። ትርጉሙ ምንድን ነው? 

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መንፈስ ቅዱስ በተለያየ ስም ይጠራል። ለምሳሌ አንዳንድ ጊዜ የኢየሱስ መንፈስ የሐዋ. 16፡7) ወይም እግዚአብሔር መንፈስ በፀኤ 31፡3) በመባል ይጠራል። ነገር ግን ተቀዳሚ ስሙ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው። ይህ ስም መንፈስ ቅዱስን በተመለከቱ ሦ ለት የተላያዩ እውነቶች ላይ ያተኩራል። 

1. መንፈስ

መንፈስ ቅዱስ የሚለው ስም የመጀመሪያ ክፍል «መንፈስ» በሚል ስም ላይ ያተኩራል። በዕብራይስጥ፥ በግሪክና በአማርኛ «መንፈስ» የሚለው ቃል የመጣው ትንፋሽ ወይም «ነፋስ» ከሚለው ቃል ነው። ይህ ቃል ከእግዚአብሔር ጋር አዛምደን ስናየው በታላቅ ኃይል የሚንቀሳቀስ የብርቱ ሩስ ሥዕል በአእምሮአችን ለመፍጠር አገልግሏል። አሳቡ ታላቅ የእግዚአብሔር ኃይል በተግባር ላይ መዋሉን የሚያሳይ ነበር። 

መንፈሳዊ ጭብጦች እንደ ነፋስ በዓይን የማይታዩ ናቸው። አናያቸውም። አንነካቸውም። ብዙ ጊዜ መኖራቸውንም እንኳ አናውቅም። እንደ ነፋስ መንፈሳዊ ጭብጦች መኖራቸውን የምናውቀው በተግባራቸው ነው። ነፋስ በሚነፍስበት ጊዜ ፊታችንን በመንካቱ ወይም የዛፎችን ቅጠሎች በማንቀሳቀሱ እናውቀዋለን። ነፋስ በታላቅ ኃይል በሚነፍስበት ጊዜ ፍችን ካሥራቸው ይነቅላቶዋል። የቤት ክዳን ቆርቆሮዎችን ይነጥላል። በተመሳሳይ ሁኔታ መንፈሳዊ ጭብጦችን የምናረጋግጠው ሰው ስዊድንበት፡ በሚፈወስበት ወይም ሕልዎ በሚያይበት ጊዜ ነው። 

የታላቅ ነፋስን አሳብ አንድ አካላዊ ህልውና ካለው ነገር ጋር አዛምዶ መናገር አስቸጋሪ ነው። ይህ ጉዳይ ለእኛ አስቸጋሪ ቢሆንም እንኳ ላጥንት ሰዎች አስቸጋሪ አልነበረም። መንፈስ የሚለው ቃል ለመንፈስ ቅዱስ ብቻ በሚሆንበት ጊዜ ምሥጢራዊ ንብረቱ የማይታይ ህልውናውን ያመለክታል። የጥንት ሰዎች ግን መንፈስ ቅዱስ ሕይወት የሌለው ነፋስ እንዳልሆነ ያውቁ ነበር። ይልቁኑ አካላዊ ህልውና ነበረው። ያፈቅር፥ ይወስን፥ ይፈርድ ነበር። ይህንን ማድረግ የሚችለው ሕይወት ያለው ነገር ብቻ ነው። 

«መንፈስ» የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ በተለያዩ መንገዶች አገልግሎት ላይ ውሏል። 

ሀ. የሰው መንፈሳዊ የሆነው ክፍል ከሥጋዊ አካሉ ተቃራኒ ሆኖ የቀረበበት ሁኔታ፡- የሰው መንፈስ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት ለማድረግ ችሎታ ያለው ቁሳዊ ያልሆነው የሰው ክፍል ነው። በኢየሱስ በማመን ሕያው እስከሚሆን ድረስ ሙት ሆኖ የሚቆየው ይህ የሰው ክፍል ነው (ኤፌ. 2፡1-6)። 

ለ. ሥጋዊ አካል የሌላቸው መንፈሳዊ ኑባሬዎች፡- መንፈሳዊ ኑባሬዎች ሕያው የሚያደርጋቸው ባሕርያት በሙሉ ያላቸው እንጂ ሕይወት እንደሌላቸው እንደ ፋላ ወይም ሥጋዊ አካል ብቻ እንዳላቸው እንደ እንስሳ ፈጽሞ አይደሉም። ከሰው የተለየ የሚያደርጋቸው ሥጋዊ አካል የሌላቸው መሆናቸው ብቻ ነው። በዚህ ክፍል ውስጥ የሚጠቃለሉ ሁለት ዋና ኑባሬዎች አሉ። 1. የተፈጠሩ መንፈሳዊ ኑባሬዎች፡- መጽሐፍ ቅዱስ አካላዊ ተፈጥር የሌላቸውን ኑባሬዎች በውሉ እግዚአብሔር እንደፈጣራቸው ያስተምረናል። እነዚህ መንፈሳዊ ኑባሬዎች መልካም (ከተለያዩ ዓይነት መላእክት እንደ አንዱ) ወይም ክፉ (እንደ ሰይጣን እና አጋንንት) ሊሆን ይችላሉ (ማስታወሻ፡- ሰይጣን በእግዚአብሔር ላይ በማመጽ በኃጢአት ክመውደቁ በፊት መልካም ከሆኑት መላእክት አንዱ ነበር። እግዚአብሔር ሰይጣንና አጋንንትን ክፉ አድርጐ አልፈጠረም።) እነዚህ መንፈሳዊ የሆኑ ኑባሬዎች ሕይወት ያላቸው ናቸው። በዙሪያችን ያሉ ቢሆኑም እንኳ ሥጋዊ አካል ስለሌላቸው በሥጋዊ ዓይናችን ልናያቸው አንችልም። አንጓንድ ጊዜ እዚህ መንፈስ የሆኑ ኑባሬዎች የሰው ቅርጽ ሊወስዱና ሥጋዊ አካል ያላቸው መስለው ሊቀርቡ ይችላሉ። በተፈጥሮአዊ አቋማቸው ቀን ሥጋዊ አካል የላቸውም። ሥጋዊ አካል የሚወስዱት ለሰው መታየት እንዲችሉ ሲፈልጉ ብቻ ነው። 

2. እግዚአብሔር፡- ሥላሴ የሆነው እግዚአብሔር መንፈስ ነው። ከዘላለም በፊት ጀምር እግዚአብሔር ሁል ጊዜ የኖረው በመንፈስ መልክ ነው። እግዚአብሔር ሁልጊዜ የኖረው መንፈስ ሆኖ ነው። ከተፈጠሩት መናፍስት በተቃራኒ እርሱ ፍጡር አይደለም። መጀመሪያም የለውም። ስለዚህ እኛ እንደምናውቀው ዓይነት ሥጋዊ ዓይን፥ ጆሮዎች ወይም እርች የሉትም። መጽሐፍ ቅዱስ እነዚህን ቃሎች ለእግዚአብሔር ሊጠቀምበት እግዚአብሔር ነገርችን ለማየት፥ ለመስማትና ለማድረግ ያለውን ችሎታ ሥዕላዊ በሆነው የሰው ቋንቋ መግለጹ ነው። ከመጽሐፍ ቅዱስ እጅግ አስደናቂ ምሥጢራዊ እውነቶች አንዱ እንደ እግዚአብሔር አብ ከዘላለም ጀምሮ መንፈሳዊ የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ሥጋ መልበሱ ነው። በምድር ላይ ሰው ቢሆንም እንኳ ዘላለማዊ መንፈሳዊ ተፈጥሮውን ግን አልተወውም ፍጹም አምላክና ፍጹም ሰው በመሆን ለዘለዓላም በመንግሥተ ሰማይ ይኖራል (ዕብ 2፡14፥ 17፤ 4፡14-16)። 

ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ «መንፈስ» የተባለው እንደ ሰዎች ሥጋዊ አካል ስለሌለው ነው። ሰማያትንና ምድርን በፈጠረበት ጊዜ ሕይወት እንደሆነው የእግዚአብሔር «እስትንፋስ» ሥጋዊና መንፈሳዊ ሕይወት የሚሰጥ መንፈስ ቅዱስ ነው። ፋስ ባይታይም እንኳ ብርቱ እንደሆነ ሁሉ መንፈስ ቅዱስም አይታይም፡ መኖሩን የምናውቀው በሕይወታችን በሚሠራው ሥራ ውጤት ነው። 

2. ቅዱስ 

ጥያቄ፡- «ቅዱስ» የሚለውን ቃል ከመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ተመልከት። ይህ ቃል ምን ማለት ነው? 

የመንፈስ ቅዱስ ስም ሁለተኛ ክፍል «ቅዱስ» የሚለው ነው። «ቅዱስ» የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙ እጅግ አስፈላጊ ቃሎች እንዱ ነው። እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ እራሱን «ቅዱስ» ብሎ ይጠራል። ደሞም ከእርሱ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ቅዱስ እንዲሆኑ ይጠይቃል። (ዘሌዋ. 1፡44-48፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡16)። ስለዚህ ቅዱስ መሆን ከእግዚአብሔር መሠረታዊ ባሕርያት አንዱ ነው። ይህ የቅድስና ባሕርይ ለመንፈስ ቅዱስ እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ ከስሙ ጋር ተያይዞ እናገኘዋለን። 

«ቅዱስ» ወይም «ቅድስና» የሚለው ቃል የመጣው መለየት፥ መራቅ፥ ልዩ መሆን ከሚለው አሳብ ነው። በብሉይ ኪዳን አንድ እንስሳ «ቅዱስ» የሚባለው ከእንስሳት መንጋ ውስጥ ተመርጦ ለእግዚአብሔር ለመሠዋት ሲለይ ነበር። ቅዱስ የሚባል ሰው ከዓለምና ከኃጢአት ለእግዚአብሔር የተለየ ሰው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስን «ቅዱስ» ብሎ ሲጠራ በውስጡ የተካተቱ ሁለት መሠረታዊ አሳቦች አሉ። 

በመጀመሪያ፥ ልዩ የመሆን አሳብ በውስጡ አለ። እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው። ምክንያቱም በምድር ላይ የሚመላለው ምንም የለም። እርሱ ሰው አይደለም። ነገር ግን እግዚአብሔር ነው። አልተፈጠረም። ነገር ግን ዘላለማዊ ነው። የእግዚአብሔር ወይም የኢየሱስ ባሕርይ የሆኑ በሙሉ የመንፈስ ቅዱስ ባሕርያት ናቸው። በኃይሉ፥ በችሎታውና በባሕርይው ከእግዚአብሔር አብና ከወልድ በስተቀር በሰማይም ሆነ በምድር የሚመስላው የለም። 

በሁለተኛ ደረጃ ፥ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ የሆነው ከኃጢአት የተለየ በመሆኑ ነው። ኃጢአትን አድርጐ አያውቅም። በህልውናውም ሆነ በባሕርይው ኃጢአት ብለን ልንጠራው የምንችለው ነገር ፈጽሞ የለም። ስስታምነት ወይም ጥላቻ ወይም ምግባረ ብልሹነት የለበትም። ብርሃንና ጨለማ ፈጽም እንደማይስማሙ ሁሉ ቅድስናና ኃጢአትም እንደዚሁ ናቸው። fiእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እጅግ ንጹሕ ስለሆነ ኃጢአት የሆነውን ሁሉ ይጠላል። ይህ እግዚአብሔር ለኃጢአት ያለውን ጥላቻ ያስረዳል። ምክንያቱም ኃጢአት የእግዚአብሔር ቅድስና ቀጥተኛ ተቃራኒ ነው። 

ጥያቄ፡- ሀ) ስለ መንፈስ ቅዱስ ስሙ የሚያመለክታቸውን እነዚህን ባሕርያት መረዳት አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድን ነው? ለ) እንደ መንፈስ ቅዱስ ባሕርይ የሆኑ የቅድስና ባሕርያትን በሕይወትህ የምታንጸባርቅባቸውን መንገዶች ግለጽ። ሐ) ልብህን ለመመርመር አሁን ጊዜ ውሰድ። እግዚአብሔር የሚፈልገውን የቅድስና አኗኗር የማያንጸባርቅ ስሕይወትህ የተደበቀ ኃጢአት እንዳለ መንፈስ ቅዱስ እንዲያሳይህ ጠይቀው። ጽድቅ ከጐደላቸው ነገሮች ሁሉ እግዚአብሔር በኢየሱስ ደም እንዲያነላህ ጠይቀው። 

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ የመሆኑ እውነት ለእኛ ለክርስቲያኖች እንደ ማስጠንቀቂያ ሊያገለግለን ይገባል። መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን ውስጥ በሙሉ ኃይል እንዲሠራ ከፈለግን ቅዱስ መሆን አለብን። በእኛ ምትክ በቀራንዮ በከፈለው መሥዋዕት በመታመንና በኢየሱስ ደም በመንጻት በእግዚአብሔር ፊት ባላን ስፍራ ቅዱስ መሆን አለብን። ነገር ግን በተግባርም ቅዱስ መሆን አለብን። በሕይወታችን ውስጥ ከሚሠራ ኃጢአት ያለማቋረጥ መንጻት አለብን። ክዓለም የተለየ ኑሮ ለመኖር መወሰን አለብን (1ኛ ዮሐ 1፡8-9፤ 2፡5-7)። በመጨረሻ እራሳችንን ለእግዚአብሔር መለየትና እግዚአብሔር እንዲጠቀምብን እራሳችንን ለእርሱ መስጠት አለብን (ሮሜ. 12፡1-2)። 

3. እግዚአብሔር

የመንፈስ ቅዱስ ሙሉ ስም «እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው»። መንፈስ ቅዱስ ሙሉ በሙሉ መለኮት ነው። ከእግዚአብሔር እብና ከእግዚአብሔር ወልድ ጋር እኩል ነው። አምላክ የሚያደርጋቸው ባሕርያት ሁሉ መንፈስ ቅዱስም አለው። ይህ ማለት መንፈስ ቅዱስ ኃይል ያለውና ሊያደርገው የሚያቅተው አንዳችም ነገር የለም ማለት ነው። አዋቂ ነው። ነገሮችን ሁሉ በውላት ያውቃል፥ ይረዳልም። የሚማረው አዲስ ነገር ከተ የለም። በአንድ ጊዜ በሁሉም ስፍራ ይገኛል። በሰማይ፥ በምድር፥ በየትኛውም በምድር ክፍል በአንድ ጊዜ ይገኛል። በእያንዳንዱ ክርስቲያን ልብ ውስጥ ይሠራል። መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር የሆኑት የፍቅር፥ የጽድቅ፡ የቅድስና፥ የምሕረት፥ ወዘተ… ባሕርያት አሉት። እርሱ ፍጹም አምላክ ነው። 

በብሉይና በአዲስ ኪዳን አልፎ አልፎ የተጠቀሱ ሌሎች ሦስት የመንፈስ ቅዱስ ስሞች አሉ። 

ሀ. የእግዚአብሔር መንፈስ ወይም የጌታ መንፈስ 

ጥያቄ፡- የሚከተሉትን ጥቅሶች ተመልከት፡- ዘፍ 1፡2፣ ዘጸአ 31፡3} መሳ. 6፡34፤ ማቴ. 3፡16l 2ኛ ቆሮ. 3፡3። እነዚህ ጥቅሶች የእግዚአብሔር መንፈስ ምን ያደርጋል ይላሉ? 

ወደፊት እንደምንመለከተው ለመግለጽ ቀላል ባልሆነ መንገድ እግዚአብሔር ስም ስት አካላዊ ህልውና ውስጥ ያለ አንድ አምላክ ቢሆንም በሥላለ እካላት መካከል የቅርብ ግንኙነት እንዳለ መጽሐፍ ቅዱስ ያላማቋረጥ ያሳየናል። መንፈስ ቅዱስ በክርስቲያኖች ሕይወት ውስጥ ለመኖር ሊመጣ እውነታው እግዚአብሔር አብና እግዚአብሔር ወልድን ጨምሮ ሥላሴ በሙሉ በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ ሊኖሩ መምጣታቸው እንደሆነ ኢየሱስ ለመናገር የቻለው ለዚህ ነበር (ዮሐ 14፡23)። ይህ የሚያመለክተው የሥላሴ አካል የሆኑት ሦስቱም በአንድነት እንደሚሠሩትና አንድ መሆናቸውን ነው። 

ይህ እውነት ከመንፈስ ቅዱስ ስሞች አንዱ በሆነው «የእግዚአብሔር መንፈስ» ወይም «የጌታ መንፈስ» በሚለው ስም ተመልክቷል። መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር አብ ጋር ካለው የቅርብ ግንኙነት የተነሣ የእግዚአብሔር መንፈስ በመባል ተጠርቷል። መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር እንደሆነ ተነግረናል። መንፈስ ቅዱስን ወደ ክርስቲያኖች የሚልከው እግዚአብሔር አብ ነው (ዮሐ 14፡26)። በኃይልና በባሕርይ እኩል ቢሆኑም እንኳ መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሔር አብ ሥልጣን ሥር ነው። ፈቃዱንም ይፈጽማል። 

ለ. የኢየሱስ መንፈስ ወይም የክርስቶስ መንፈስ 

ጥያቄ፡ የሚከተሉትን ጥቅሶች በሙሉ ተመልከት፡- የሐዋ. 16፡7፤ ሮሜ 8፡9፤ ፊልጵ. 1፡19፤ 1ኛ ጴጥ. 1፡11። በኢየሱስና በመንፈስ ቅዱስ መካከል ያለውን ቀንኙነት እንዴት ያሳዩናል? 

መንፈስ ቅዱስ አንዳንድ ጊዜ «የኢየሱስ መንፈስ» «የክርስተስ መንፈስ» ወይም «የኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ» በመባል ተጠርቷል። በሮሜ 8፡9 በተለይ መንፈስ ቅዱስ ከሌሎቹ የሥላሴ አካላት ከእያንዳንዳቸው ጋር ያላውን የቅርብ ቀንኙነት ያሳያል። በዚህ ጥቅለ መንፈስ ቅዱስ በመጀመሪያ «የእግዚአብሔር መንፈስ” ቀጥሎም «የክርስቶስ መንፈስበመባል ተጠርቷል። ይህ ጥቅስ የሚናገረው ስለ አንድ መንፈስ እንጂ ስለ ሦስት መንፈሶች ያለመሆኑ ልጽ ነው። መንፈስ ቅዱስ ከአብ ጋር እጅ በቅርበት የተዛመደ ስለሆነ የእግዚአብሔር መንፈስ በመባል ተጠርቷል። ነገር ግን ክኢየሱስም ጋር የቅርብ ቀንኙነት ስላለው የኢየሱስ መንፈስ በመባል ተጠርቷል። እንዲያውም በእርጥ ኢየሱስ የተናገረው መንፈስ ቅዱስን ወደ አማኞች እንደሚልክና በዚህ አማካይነት ኢየሱስ በሕይወታቸው እንደሚኖር ነው (ዮሐ 14፡17-18)። 

ሐ. ሰባቱ መናፍስት ወይም ሰባቱ የእግዚአብሔር መናፍስት 

ጥያቄ፡- ራእ 14 ። 4፡4 እና 5፡6 አንብብ። ሀ) በዚህ ስፍራ ላመንፈስ ቅዱስ ምን ስም ተሰጠ? ለ) መንፈስ ቅዱስ ይህ ስም የተሰጠው ለምን ይመስልሃል? 

በራእይ መጽሐፍ ያልተለመደ የመንፈስ ቅዱስ ስም እናገኛለን። ጦርሶ ያለተላመደ በመሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን እንዴት መተርጐም እንዳለበት እንኳ እርግጠኞች አይደሉም። አንዳንድ ምሁራን «ሰባቱ መናፍስት» ተብሎ መተርጐም አለበት ሲሉ አሉች ደግሞ «ሰባቱ ∫እግዚአብሔር መናፍስት» ተብሎ መተርጐም አለበት ይላሉ። ዮሐንስ በራእይ የሚናገረው ምን ነበር? ሰባት የተለያዩ መናፍስት ነበሩን? ወይስ ሰባት ክፍሎች ያሉት እንድ ወመንፈስ ነበር? የሁለቱም ጥያቄዎች መልስ አይደለም ይሆናል። ዮሐንስ ስለ መንፈስ ቅዱስ የሰጠውን ይህን ስም ለመረዳት የራእይ መጽሐፍን ባሕርይ መረዳት አለብን። ራእይ «አፖካሊፕቲክ» (ተምሳሌታዊ አጻጻፍ) የሚባል የሥነ ጽሑፍ ዓይነት የያዘ ጽሑፍ ነበር። በእንደዚህ ዓይነቱ ጽሑፍ ጸሐፊው ትርጉምን ለማስረዳት ብዙ ጊዜ ምልክቶችን ይጠቀማል። ለዚህ ነው የራእይ መጽሐፍ እጅግ ጥልቅ ትርጉሞች ባሏቸው በምልክታዊ ራእዮች የተሞላው። በተምሳሌታዊ ጽሑፎች አይሁዶች አንዳንድ ትርጉሞችን በሥዕላዊ መግላማነት ለማቅረብ ቁጥርችን ይጠቀማሉ። በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ቁጥር 2 ና 7 ያለማቋረጥ ይደጋገማሉ። ለአይሁዶች ሰባት ቁጥር የሚያሳየው ሙሉነትን፥ ፍጹምነትንና ታላቅነትን ነው። ስለሆነም ዮሐንስ ይህን ስም ለመንፈስ ቅዱስ በመጠቀም የሥላሴ አካል የሆነውን መንፈስ ቅዱስ ፍጹምነት፥ ታላቅነት፥ ብርታትና ችሎታ ማሳየቱ ነበር።

ምንጭ፡- “የመንፈስ ቅዱስ የጥናት መምሪያና ማብራሪያ”፣ በቲም ፌሎስ ተጽፎ፣ በጌቱ ግዛው የተተረጎመ እና በኤስ አይ ኤም ጽሑፍ ክፍል የተዘጋጀ ነው፡፡ ለዚህ ድንቅ አገልግሎታቸው እግዚአብሔር ይባርካቸው፡፡ ይህን ጽሁፍ ኮፒ እና ፕሪንት አድርጎ መጠቀም ይቻላል፤ ሆኖም ጽሁፉን መለወጥና ለሽያጭ ማዋል በሕግ የተከለከለ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.